የኢትዬጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 13.6 ቢልዬን ብር (400 ሚሊዬን ዶላር) ዘመናዊ የህክምና ማዕከል እያስገነባች ትገኛለች

ቅድስት ቤተክርስቲያን 13.6 ቢልዬን ብር (400 ሚሊዬን ዶላር) ዘመናዊ የህክምና ማዕከል እያስገነባች ትገኛለች ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በአይነቱ አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ እና የሀገሪቷን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ያደርጋታል ተብሎ የሚጠበቅ የማስተማሪያ የህክምና ማዕከል የኢትዬጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እያስገነባች ትገኛለች። በ400ሚሊዬን ዶላር (13.6 ቢሊዬን ብር ) ወጪ ወቶበት የሚገነባው ይህ የህክምና ማዕከል በ210ሺህ ካሬ ስፋት ላይ የሚያርፍ ነው ። የህክምና ማዕከሉ ስያሜም “ተዋህዶ ዲፕሎማቲክ ሜዲካል ሲቲ” የሚል መጠርያ ያለው ሲሆን በአንድ ጊዜ 600 ተኝቶ ታካሚያንን ማስተናገድ የሚችል ማዕከል ነው። ከህክምና መስጫነት በተጨማሪም የህክምና ማስተማርያ የትምህርት ተቋምን ያካተተው ይህ ማዕከል አለም የደረሰችበት ረቂቅ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የህክምና ማዕከሉ በ2015 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የሀገሪቷን የህክምና ቱሪዝም እንቅስቃሴ ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል። ግንባታው በጉለሌ ክፍለከተማ እንጦጦ ተራራ ላይ የሚገነባ ሲሆን ግንባታውም የአለም አቀፍ ህንፃ ተቋራጭን መስፈርት በሚያሟላው በሌጀንደሪ ሜጋኮርፕ ህንፃ ተቋራጭ የሚገነባ ነው። በማዕከሉ የሚገነቡ ህንፃዎች የተኝቶ መታከሚያ ፣ግዙፍ የፅኑ ህመሟን ማዕከል ፣የድንገተኛ ክፍል ፣ የመማርያ ክፍላት ፣የመፀበያ ስፍራ ፣የማምለኪያ እና የፀሎት ስፍራ እንዲይዝ ታስቦ ዲዛይን የተሰራለት ነው።
ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት ሲጀምር በውጪ ሀገራት በከፍተኛ የህክምና ባለሞያነት የሚያገለግሉ የስላሴ ልጅ የሆኑ ባለማህተብ ሀኪሞች ወደ ማዕከሉ እንደሚጡ የሚደረጉ እንደሚሆን የሚታሰብ ሲሆን ከእዚህ በተጨማሪም ቅድስት ቤተክርስቲያን በሀገር ውስጥ ያሉትን በህክምና ዘርፍ የተሰማሩ የቅድስት ስላሴ ልጅ የሆኑ ባለሞያዎች በመጠቀም የሚመራ ተቋም ነው።
@EOTCKahinatUSA 

Leave a Reply