የኢትዮጲያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን በሩብ አመቱ 120 ቶን ተቆልቶ የተፈጨ የኤክስፖርት ቡና የጥራት ማረጋገጫ ለማግኘቱን ገልጸ፡፡

የቡና እና ሻይ ባለስልጣን በሩብ አመቱ አፈጻጸም የመደበኛና የካፒታል በጀት አጠቃቀም የሩብ አመቱ በመከፋፈል እንዱሁም የተቋሙ የኦዲት ግኝት ምልከታ የፋይናንስ መረጃዎችን ትክክኛነት በየሩብ አመቱ ኦዲት ያደርጋል፡፡

በዚህም የመረጃዎችን ተጨባጭነት፤ ታማኝነትና ትክክለኛነት የፋይናንስ ደንቡን ተጠብቆ እየተከናወነ መሆኑን በማረጋገጥና በማቅረብ በተያዘው እቅድ መሰረት እየተከናወነ መሆኑ በጥንካሬ ተጠቅሷል፡፡የወጪ ንግድን በሚመለከትም ለቋሚ ኮሚቴው በቀረበ ሪፖርት መሰረት በእቅድ ከተያዘው እንጻር ዝቅተኛ አፈፃጸም የታየበት እና ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጲያ ከቡና ንግድ ከውጪ የምታገኘዉ ምንዛሬ የኢኮኖሚው ዋልታ እንደመሆኑ ቋሚ ኮሚቴዉ የወጪ ንግድ ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

የባህላዊ የቡና ምርት እና አቅርቦትንም በሚመለከት የበሽታ መከላከል እና ቁጥጥሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተመላክቷል፡፡

በሩብ አመቱ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በእቅድ 120 ቶን የተፈጨ የኤክስፖርት ቡና አስፈላጊው የጣዕም ምርመራ ተደርጎለት የጥናት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዲያገኝ የተሰራበት መንገድ ከእቅዱ በታች አፈጻጸም የታየበት በመሆኑ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

ዘጋቢ ቤዛዊት ግርማ

ቀን 22/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply