የኢትዮጲያ አየርመንገድ በናይጄሪያ አዲስ ብሔራዊ አየርመንገድ ለማቋቋም በአጋርነት ተመረጠ፡፡የናይጄሪያ መንግስት አዲስ ብሔራዊ አየርመንገድ ለማቋቋም የኢትዮጲያ አየርመንገድን በአጋርነት መርጦ…

የኢትዮጲያ አየርመንገድ በናይጄሪያ አዲስ ብሔራዊ አየርመንገድ ለማቋቋም በአጋርነት ተመረጠ፡፡

የናይጄሪያ መንግስት አዲስ ብሔራዊ አየርመንገድ ለማቋቋም የኢትዮጲያ አየርመንገድን በአጋርነት መርጦታል፡፡

የኢትዮጲያ አየርመንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እንደተናገሩት፣ የናይጄሪያ መንግስት ባወጣው ጨረታ የኢትዮጲያ አየርመንገድ የተሳተፈ ሲሆን በአጋርነት መመረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ ልከዋል፡፡

በናይጄሪያ ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር የሚመራ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከኢትዮጲያ አየርመንገድ ማኔጅመንት አባላት ጋር በሳምንቱ መጀመሪያ መወያየታቸውን አቶ መስፍን ገልጸዋል፡፡

ናይጄሪያ ኤር ተብሎ አዲስ የሚቋቋመው የናይጄሪያ ብሔራዊ አየርመንገድ የናይጄሪያ መንግስት ከ5 በመቶ የማይበልጥ ድርሻ እንደሚኖረው የኢትዮጲያ አየርመንገድ 49 በመቶ የተቀረው 46 በመቶ ለናይጄሪያውያን ባለሀብቶች የሚያዝ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

“ የተወሰነ ድርሻ በባለቤትነት ይዘን በጋራ ለመስራት ነው ያሰብነው ፡፡ ቀጣይ የሚቀር ድርድር አለ፡፡ “ ብለዋል፡፡ የናይጄሪያ አቪየሽን ሚኒስትር በመጪው ሳምንት ውሳኔውን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ናይጄሪያ በተፈጥሮ ዘይት ምርት የምትታወቅ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ሀገር ብትሆንም ብሔራዊ አየርመንገድ የላትም ፡፡

ናይጄሪያ ኤርዌይስ ፤ ቨርጅን ናይጄሪያ እና ኤር ናይጄሪያ የተባሉ አየርመንገዶች በተለያየ ጊዜ አቋቁማ የነበረ ቢሆንም ሁሉም ፈርሰዋል፡፡

ከአፍሪካ በአንደኝነት በአለም 24ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ትርፋማ የሆነው የኢትዮጲያ አየርመንገድ በቶጎ ሎሜ ፤ በማላዊ ፤ ዛምቢያ ፤ ሞዛምቢክ ፤ ቻድ እና ኮንጎ አየርመንገዶችን በጋራ በማቋቋም ሰፊ ልምድ አካብቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 07 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply