የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የባለሀብቶችንና የአርሶ አደሮችን ንብረት እየዘረፈ ላለው የሱዳን ጦር አስተማሪ የአፀፋ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 12 ቀ…

የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የባለሀብቶችንና የአርሶ አደሮችን ንብረት እየዘረፈ ላለው የሱዳን ጦር አስተማሪ የአፀፋ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀ…

የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የባለሀብቶችንና የአርሶ አደሮችን ንብረት እየዘረፈ ላለው የሱዳን ጦር አስተማሪ የአፀፋ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስት በካሃዲው ትህነግ ላይ እርምጃ መወሰዱን ተከትሎ የሱዳን ጦር በጎን በምዕራብ አርማጭሆ እና በመተማ ኃይሉን በማስጠጋት ምሽግ ሲቆፍር እና በባለሀብቶች ላይ ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱ ይታወሳል። የመንግስት ዝምታ የልብ ልብ የሰጠው የሱዳን መከላከያ ሰራዊት ከሰሞኑም በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብደራፊ በኩል ሰላም በር እና በጠረፍ ወርቅ ቀበሌ ስናር እና መሰረት መቅረጫ አካባቢ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመዳፈር ከባድ መሳሪያ ጭምር በባለሀብቶችና አርሶ አደሮች ላይ በመተኮስ የእርሻ ካምፖችን በመቆጣጠር የለየለት ዘረፋ ውስጥ መግባቱን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። ይህ የሱዳን የወረራ አካሄድ መንግስት ከትህነግ ጋር በነበረው ጦርነት ተዳክሟል፣ ጦር የለውም ብለው የነገሯቸውን የተሳሳተ መረጃ ከመስማታቸው ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የገለፁት በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የጠረፍ ወርቅ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ስመኘው ብርሃኔ ናቸው። አቶ ስመኘው እንደገለፁት አሁን ላይ በመንግስት በኩል ለሱዳን ጦር ተገቢ የአፀፋ ምላሽ እየተሰጠ አይደለም። በዚህም አብደራፊ አካባቢ በሰላም በር፣ በመሰረት መቅረጫና በስናር በኩል ተጨማሪ ኃይል በማስጠጋት በበርካታ ባለሀብቶችና አርሶ አደሮች የእርሻ ካምፕ ላይ የቡድን መሳሪያዎችን ጭምር በመተኮስ ዓመቱን ሁሉ የደከሙበትን የደረሰ ሰብል እንዳይሰበስቡ አድርገዋል፤ ቦታውን በመቆጣጠርም በጎን ተሽከርካሪ አቅርበው እየጫኑ ወደ ሱዳን እየወሰዱ መሆናቸውም ተገልጧል። የአካባቢው ሚሊሻና ልዩ ሀይልም ከግብአት ጋር በተያያዘ ውስንነት እንዳለበት የተናገሩት አቶ ስመኘው መንግስት ትኩረት ሰጥቶ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል። በቅርብ ቀን ምላሽ የማይሰጥበት ከሆነ ግን ሉአላዊነቱ ሲደፈርና ከእርሻ ማሳው ያለማንም ተከላካይ እየተፈናቀለ ያለው አርሶ አደር ባለው መሳሪያ መግጠሙ እንደማይቀር መታወቅ አለበት ብለዋል። በዛሬው እለትም ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በስናር የእርሻ ልማት ቀጠና በኩል በእነ አቶ ባሻ ጥጋቡ የእርሻ ካምፕ ማሽላ ለማራገፍ ደጋጋ ይዘው በሄዱ ሰራተኞች ላይ ተኩስ በመክፈት እንዳሳደዷቸውና የሱዳን ጦርም በአካባቢው ስለመስፈሩ ሰምቻለሁ ብለዋል። በመንግስት በኩል የተወሰኑ የሰራዊት አባላትና ጥቂት ሚሊሻዎች የሚለው ነገር አልተዋጠልንም ያሉት አቶ ስመኘው መሬት ላይ የሚታየው እውነታ ግን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሱዳን የመከላከያ ጦር ባልተለመደ መልኩ ኃይሉን ሲያስጠጋና ሲገባ እየተስተዋለ ነው ብለዋል። በዲፕሎማሲ በኩል የሚሰራው እንዳለ ሆኖ በቂ የሆነ ዳር ድንበርን የሚያስከብርና ለጠላት ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ የመከላከያ ሰራዊት ማስፈር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፤ ያልተገባ ዋጋ እየተከፈለ ነው ሲሉም ጥሪ አድርገዋል። ሙሉ ዝግጅቱን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply