የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትን እየተጋፋ ያለው የሱዳን ጦር  በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በንጹሀንና አርሶ አደሮች ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ…

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትን እየተጋፋ ያለው የሱዳን ጦር በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በንጹሀንና አርሶ አደሮች ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ…

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትን እየተጋፋ ያለው የሱዳን ጦር በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በንጹሀንና አርሶ አደሮች ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ባህር ዳር የአሻራ ሚዲያ ያነጋገራቸው አቦጢር’ በተባለ አካባቢ በእርሻ ኢንቨስትመንት ተሰማርተው የሚኖሩ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት ከፍተገኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ብለዋል ። ተስፋፊውና ዘራፊው የሱዳን ጦር ከታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ዲሽቃ፣መትረ ጊዬስ፣ብሬንና ሌሎች መሳሪያዎችን በመጠቀም ቃጠሎ እና ዝርፊያ ከፈፀመባቸው መካከል የምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ምድረ ገነት/አብደራፊ ነዋሪዎች ዋና የችግሩ ሰለባ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ሱዳኖች የእርሻ ካምፓቸውን ከርቀት ሆነው በከባድ መሳሪያ በመምታት አውድመዋል፤ ቀርበውም የተለያ መሳሪያዎችን ወስደዋል እንዲሁም 3000 ኩ/ል የሚሆን ማሽላን በመዝረፍ በመኪና ጭነው ወስደዋል ብለዋል ነው ያሉት ነዋሪዎቹ። አቦጢር፣ ስናር፣ወዲ ከወሊና፣ መሰረት መቅረጫ በተባሉ እና በሌሎችም የልማት ቀጠናዎች ከ በርካታ ባለሀብቶች የችግሩ ተቋዳሽ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ ሱዳኖች እያሳዩት ካለው ከወትሮው ለየት ያለ እንቅስቃሴ መረዳት የቻልነው አጉል ተስፋ የሰጣቸው አካል እንዳለ ነው ያሉት ነዋሪዎች ድሮም ከሱዳን ጋር ቅርርብ የነበራቸው ኮሎኔል አባዲ የተባሉ የትህነግ ሰውን ጨምሮ አያሌ የስርዓቱ አመራሮች፣ ዘር አጥፊው ሳምረ፣ልዩ ሀይሉና ሚሊሻው በሱዳን እንደሚገኙ ይታወቃል ነው ያሉት ነዋሪዎች። እንደምንጫችን ገለጻ የሱዳን ጦር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደገባ እያወቅን፣ ተወረን፣ተዘርፈንና ከልማታችንም ተደናቅፈን እንኳ መንግስት ከሱዳን ጋር ተነጋግሮ መፍትሄ ያመጣል በሚል ጉዳታችን አሳውቀን በትዕግስት እየጠበቅን እንገኛለን ሲሉ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል። የሱዳን ጦር ለአርሶ አደሩና ለሚሊሻው ሁሉ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ወደ ወረራ፣ተራ ዝርፊያና ስርቆት መሰማራታቸው እየታወቀ በኢትዮጵያ በኩል ጥቃት ተፈፀመብኝ በማለት አልጀዚራን ጨምሮ በብዙ ሚዲያዎች ፕሮፖጋንዳ እንደምትሰራ የሚታወቅ ስለመሆኑም ምንጫችን አስረድተዋል። በመጨረሻም መንግስት ከሚያደርጋቸው ህግን የማስከበር እርምጃወች ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ሉአላዊነትን ማስከበር የሚችል ጦር ማሰማራት እንዳለነት ነዋሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply