የኢትዮጵያን ቋንቋ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያስተዋውቁት ሰው

ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ በመጣው የኢሕአዴግ ስርአት የቋንቋ ጉዳይ ዋናው የፖለቲካው ማጠንጠኛ ሆኖ ቆይቷል። በተለይ ከቋንቋው ጋር ማንነትን ወይም ብሔርን መሠረት በማድረግም የፖለቲካ ስርአቱን አጠነከረው። ይህን ተከትሎም ሁሉም በራሱ ቋንቋ እና ማንነት ውስጥ ገብቶ የትልቋ ኢትዮጵያ ምስል እየደበዘዘ መጣ። ብሔራዊነት እየኮሰመነ፣ ክልላዊነት እና አካባባዊነት ጎልብቶ መጣ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና፣ የብዙ ኮር ዲፕሎማቲክ ኮሚኒቲ መቀመጫ ከመሆንዋም በተጨማሪ በውጭ አገር ሰዎች ዘንድ ትልቅ አገር እንደሆነች ይነገርላታል። ኢትዮጵያ እንደ ትልቅነትዋ የሚመጥን የውስጥ ፖለቲካዋ መስተካከል እንዳለበት ይነገራል። በተለይ ቋንቋ ከመግባቢያት አልፎ ፖለቲካ የሆነባቸው አገራት ብዙ ችግሮች ውስጥ ገብተዋል። ሰለዚህ የብሔራዊ ቋንቋ ፍልስፍና ላይ ምሁራን ሊሰሩበት እንደሚገባ ይነገራል። በዛሬው ኢትዮጵያዊ ስንክሳራችን፣ የኢትዮጵያን ቋንቋ ለአለማቀፉ ሰው ለማስተማር ብርቱ ጥረት እያደረጉ ስላሉ ሰው እናወጋችኋለን።

አዘጋጅ:ጥበቡ በለጠ

ቀን 30/04/2013

ኢትዮጵያዊ ስንክሳር

Source: Link to the Post

Leave a Reply