የኢትዮጵያን የቡና ባህል የሚያሳይ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-b9a2-08db2a4563ba_tv_w800_h450.jpg

የኢትዮጵያን ማኅበረሰብ የቡና ባህል የሚያስቃኝ በዓይነቱ የመጀመሪያ መሆኑ የተነገረለት አውደ ርዕይ ከቀናት በፊት አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል።

በአውደ ርዕዩ ላይ የተለያዩ አካባቢዎች የቡና አፈላል ሥርአት እና ባህላዊ ትውፊቶች ለታዳሚያን ቀርበዋል፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በቡና መድረክ ላይ የተለያዩ ሰዎች የሚሰባሰቡ ሲሆን፣ በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግባራትም ይከናወናሉ፡፡

“ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ ከመነጣጠል ይልቅ በአንድነት መኖርን የሚፈልግ ስለመሆኑ ማሳያ ነው” ሲሉ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው በሥነ ስርአቱ ወቅት ባሰሙት ንግግር ተናግረዋል፡፡

ይህን ባህል ሥርዓት በዩኔስኮ የማስመዝገብ ዓላማ በማንገብ አውደ ርዕዩን መጀመራቸውን የገለጹት ደግሞ የአዘጋጁ ዋርካ ኮፊ የተባለ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሰዓዳ ሙስጠፋ ናቸው፡፡

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply