የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ያሳድጋል የተባለለት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡ዲጂታል የክፍያ ስርዓትን የሚከተሉ ከ30 በላይ ተቋማት የሚሳተፉበት የዲጂታል ፋይናንስ ማሳያ ኢትዮጵ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/abkL9MtJb5oMh0vAaFnjIMUjUYqjGVKkdVB_tI7LcMstFOZIENDSHoL5xO9lI8J79IZe_mjRWkVUixKyfQ-aLlMfqRygmEKPke1H78KeSXrLN1U19SnD3X7uFl1YY3MBxEBmbsWTYkUf2st188lZAnJ7klzn1TD8f6qz7Nsa16sDYhfsjG77nVmcVXdVZiDr9H8XuTFJ7cMpSD8nUxW1sPdIE-fq4y98fK8Pc-tX06oVVmzjIc68FINSEO4yNWPqP1PRa2A2YupmDza4V_lkLvTG6oFXrfCaWyLPa9-cg9TTOt9BC0-3IxuFyCu_0CxNISUfCe-vIWlpGJVZKai8fw.jpg

የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ያሳድጋል የተባለለት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡

ዲጂታል የክፍያ ስርዓትን የሚከተሉ ከ30 በላይ ተቋማት የሚሳተፉበት የዲጂታል ፋይናንስ ማሳያ ኢትዮጵያ 2022 ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ከተማ ተከፍቷል፡፡

ኤግዚቢሽኑ አገራችን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ እየሄደችበት ላለው ጉዞ ለመደገፍ ትልቅ ፋይዳ እንዳለዉም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

የዲጂታል ፋይናንስ የስራ ቡድን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዩሴፍ ክብረት በዘርፉ ያሉ ችግሮች ላይ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያመነጩ ይረዳል፤ በአገራችን የዲጂታል ገበያው እንዲሳለጥ ማህበረሰቡ ስለ ዲጂታል ፋይናንስ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረውም ገልጸዋል፡፡

በኤግዚብሽኑ ላይም ባንኮች፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት፣ የክፍያ ሥርዓት ኦፕሬተሮች፣ የሃዋላ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደተሳተፉበትና በኤግዚቢሽኑ ላይም በአገሪቷ የሚገኙ በቴክኖሎጂ የታገዙ የፋይናንስ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ከ30 በላይ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎታቸውን ለእይታ ማቅረባቸዉ ታዉቋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 09 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply