የኢትዮጵያን የፀጥታ ሁኔታ የሚያውኩ አካላት የፖለቲካ ፍላጎት የማሳኪያ ልምምድ የሌላቸው ናቸው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህንን ይህንን ያሉት በአሁን ሰዓት በመካ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/rI9qKqavXKMNEn6TJrLZeqLDoPZamKtjfe8EJgy1DB6kDsK55da1rDpVgaYO1YVM4lXKDQm3ACTcYCMafMiRn7VDS69CRtZByrGJMRdrRHIds-o4QpgB9zrRIGAs0UUPqxC23TxcB7CetneL1T4EzOH_BTJ-LWzLs9kaSpFK7vml0uB6dfRGpmmBiOn5kreFBw0NpqHs0XwtePcGGqWXaovW6abg4yW5xrrs3dGkaQJeN-xlrAzqNkZzAE6v13SVpc0h4nFCkatXXlqjFY4K4e2Y-XQKPmNuWAmHyAluN9wzXVyTtCQFlmoivk2B52ZFHLdwAeu_tChHCAm7cG63Kg.jpg

የኢትዮጵያን የፀጥታ ሁኔታ የሚያውኩ አካላት የፖለቲካ ፍላጎት የማሳኪያ ልምምድ የሌላቸው ናቸው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህንን ይህንን ያሉት በአሁን ሰዓት በመካሄድ ላይ በሚገኘው ኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላምን በተመለከተ ካነሷቸዉ ነጥቦች መካከል
•የኢትዮጵያን የፀጥታ ሁኔታ የሚያውኩትአካላት የፖለቲካ ፍላጎት የማሳኪያ ልምምድ የሌላቸው ናቸው፡፡
ከሸኔ ጋር በታንዛንያ የተደረገው ድርድር ያለ ውጤት በመጠናቀቁ ምክንያት ምንምለህዝብ ይፋ ማድረግ የተቻለ ነገር የለም ብለዋል፡፡
•እነዚህ አካላት በቀላል ሊፈታ የሚችል ጉዳይ ሁሉ ወደ ግጭት ይወስዱታል፡፡
•ከጦርነት ምን አተርፍን ከሰላም ምን አተረፍን ተብሎ መጠየቅ ቢገባውም የሚጠየቀው የሰላም ድርድር ምን አምጣ የሚል ነው፡፡
•በለውጡ ዋዜማ በውጭ የነበሩ ነፍጥ አግብው ሲታገሉ የነበሩትን ፓርቲዎች ወደ ሀገር እንዲመጡ ጥሪ ስናቀርብ ለኦነግም ተመሳሳይ ጥሪ ነው ያደርግነው እንጂ የተለየ አልተደረግም የተለየ ነገር አለ ብለው የሚያስቡት ነገሮችን በሴራ የሚመለከቱ አካላት ናቸው፡፡
•ሸኔ አሁን ጫካ የገባው በሰላማዊ ትግል ችግር ሊፈታ አልቻለም ብሎ ቢሆን እንኳን እያደረገው ያለው መኪና ማቃጠል፣ቤት ማቃጠል፣ማገትና ሰው መግደል እታገልለታለው የሚለው ህዝብ ማሰቃየት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አቤል ደጀኔ
ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply