የኢትዮጵያን የፊልም ኢንደስትሪ እንደሚቀይሩ ተስፋ የተጣለባቸው ሶስት አዳዲስ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገቡ።ኘሮጀክቶቹም ዓመታዊ የፊልም ሽልማት ፣የቀጥታ ፊልም ስርጭት አገልግሎት እና አ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/F_S7KTxivJ5mpuQeEGgu0AmtdS6ueD0MiFsfPsbCyvISrk8XfFXXlIlGNPPnC8u6e26KtUcD6g6ImheD32EuvV1jM1t_2ME2QxcjiwVAiPtnEJVcJrp969r6q1AvsaH4OkvezIkA1NZWsg0AhvhfcT3mKruv_knW5vCdW3qUVVKfIUV11_wHTwKgcOQWmYg6mJ64t8AkHfzVmc4pBMQV6zv9_pK6RunAUzh7_x87WsG0_-PA2JSPvD6w9ZlRWPs6M3R0qFWoljM0JoHGmjWJBp2nHCa4CvCp7Pgtz52YtgsNHxwJsdSjPCKSzrpzQntxGlR3HROlKpqebKiEDwxdsg.jpg

የኢትዮጵያን የፊልም ኢንደስትሪ እንደሚቀይሩ ተስፋ የተጣለባቸው ሶስት አዳዲስ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገቡ።

ኘሮጀክቶቹም ዓመታዊ የፊልም ሽልማት ፣የቀጥታ ፊልም ስርጭት አገልግሎት እና አዲስ የፊልም ከተማ የተባሉ ናቸው።

ፕሮጀክቶቹን ነድፎ ወደ ስራ ለማስገባት አምስት አመታት እንደፈጀ የአርክ ውድስ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አርሴማ ወርቁ በምርቃቱ ወቅት ተናግረዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸው በአለም ዙሪያ የኢትዮጵያን የፊልም ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እንደሚረዳና የሌሎችንም ሀገራት ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

ሶስቱ አዳዲስ ኘሮግራሞች ማለትም አርክ ውድ አዋርድ (ሽልማት )በየአመቱ በፊልም ኢንድስትሪው በተለያዩ ዘርፎች የተመረጡ ስራዎች እና ባለሙያዎች ተመዝነው እውቅናና ሽልማት የሚያገኙበት ይሆን ዘንድ ወደ ስራ ገብቷል።

ሁለተኛው እና የቀጥታ ስርጭት ሂደትን ተከትሎ ወደ ስራ የገባው አርክውድስ ሙቪስ( የቀጥታ የፊልም ስርጭት) በኦንላይን ፕላትፎርም የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።

የቀጥታ ስርጭት ማሰራጫው ለኢትዮጵያ ፊልም አፍቃሪያን የፊልም ማሳያ መድረክ ብቻ ሳይሆን፣ የባለሙያዎችን የቅጂ መብት የሚያስጠብቅና የፊልም ስራዎችም ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

አርክውድስ በሶስተኛነት ያስጀመረውን (አዲስ የፊልም ከተማ) ኘሮጀክትን ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጀት ላይ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን፣ በዚህ ኘሮጀክት ጥራት ያላቸው የኢትዮጵያ ፊልሞችን ለመስራት የሚያስችል የፈጠራ ማእከል ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል ተብሏል።

በየዉልሰዉ ገዝሙ
ጥቅምት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply