
ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ናቸው የተባሉ የ27 ሰዎች አስከሬን በደቡብ አፍሪካዊቷ አገር ዛምቢያ መዲና ሉሳካ አቅራቢያ መንገድ ዳር “ተጥለው” እሁድ ዕለት መገኘታቸው ተነገረ። ከዋና ከተማዋ በስተሰሜን በሚገኘው ንግዌሬሬ በተባለው አካባቢ መንገድ ዳር ተጥለው የተገኙት አስከሬኖች አገሪቱን አቋርጠው ይጓዙ የነበሩ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። ፖሊስ ከተገኙት አስከሬኖች ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተነግሯል።
Source: Link to the Post