የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሲኖዶሱ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የ2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መጠ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/eRDXDaKTUXCYdHm_2kGvXJ_21NhCouc7kM7S5NT0n16aEJhZ4SctE1DUv2RtKoCygH7glJ4FJxCfLb9KtzibXQv2ZRXez0P2AfsRmHRaeLVih6y7iaCgVKJ5bLODv9x4orZKa4WHuDhISVbMuoEF8CekxVbgxmWOmHHMfKOZNoqgw77Zi0b2VmtKvIWipt11aOfKTRJbqg7u73iWtqSplbmAwQMSX86tbGE_LcPif3FjdS5HtON7TaW5VjkdfGXIYMoc8q_T2inD9yiioS1R6i5NODIduKEK5jMjbEyUlBxS_5vGmpHSShaUa5qUs7iOH00_OiVT2-7ubxeqxxydPw.jpg

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሲኖዶሱ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የ2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መጠናቀቅን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ በምክክር ኮሚሽኑ ላይ ቅሬታ እንዳለው አሳውቆ ነበር፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ “የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ አኳያ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን” ጉባኤው መረዳቱን ገልጾ ቤተክርስቲያኒቱ በኮሚሽኑ በኩል በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ እንዳልተደረገላት በመግለጽ በሂደቱ ቅር መሰኟቷንና ከዚህም በመነሳት “የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ” ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙንም መግለጫው ያትታል፡፡

የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በበኩሉ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልጾ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም በዚያው በኩል እየተሳተፈች መሆኑን አብራርቷል፡፡

ሆኖም ቅሬታዎችን ለማጥራትና አብሮም ለመስራት ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር ቅዱስ ሲኖዱሱ ጽ/ቤት ድረሰ በመገኘት ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ይህ የአካታችነት መርህ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር በእኩልነት የሚተገበር መሆኑንም ጨምሮ ገልጧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply