የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ ሸበሌ የተባለችው መርከብ በርበራ ወደብ ላይ መድረሳ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አሸብር ሉታ ለአሀዱ እንዳሳወቁት ጊቤ የተሰኘችው የኢትዮጽያ የመጀመሪያዋ መርከብ  ከ 20 ቀናት በፊት 11ሺህ 200 ሜትርክ ቶን የፍጆታ እቃ ለሶማሌ ላንድ ገበያ ማጓጓዟን አስረድተዋል።

አቶ አሸብር አክለውም ሸበሌ የተባለችው የኢትዮጵያ ሁለተኛዋ መርከብ በተጨማሪ ከ11ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ስኳርና ሩዝ ይዛ በርበራ ወደብ መድረሷን ያነሱ ሲሆን መርከቧ ከህንድ የጫነችውን ስኳርና ሩዝ በመያዝ የበርበራ ወደብ ላይ ማራገፍ እንደቻለች ጠቁመዋል።

በበርበራ ወደብ ላይ  የተጀመረው አገልግሎት የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ያነሱት አቶ አሸብር  ከዚህ በተጨማሪ የሱማሌ ላንድ ነጋዴዎች ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸውን ተከትሎ ድርጅቱ፤ አገልግሎት መስጠቱን በመደበኛነት እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ጊቤና ሸበሌ የተባሉት መርከቦች በኮሪደሩ አገልግሎት ለመስጠት ምቹ መሆናቸውን የገለፁት ዳይሬክተሩ በነሐሴ ወር አጋማሽ ጊቤ መርከብ 15ሺ ሜትሪክ ቶን ሩዝ በመጫን በርበራ ወደብ እንደምትገባም ተናግረዋል።

ቀን 22/11/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply