የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለስራ ፈጣሪዎች ያለማስያዣ ድጋፍ ሊያደርግ ነዉ ተባለ። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀሳብ ያላቸዉ ሀሳባቸዉ ተወዳዳሪ ሆኖ ላሸነፍ እና ወደምርት ቢገቡ አዋጪ ይሆናሉ ብሎ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/lAcWz8vxFzzoZE_aIHv-qMJutgLIWoJ8GVTQf9S6yTEw5fg-oD_CiVo23sAydp-6NAYkaR69sAF8LZg-GQghr0g4ZashQzJ080SzJxJmK1ZQIygnh6XwNJNY_Rnb4V0M-Ot_Vjt9xjCW7pPWGSiuZBTRauObzyrN8ALd6NFV3ZVd7Tzy3ZSMXjRtCAkfNPWNSJSF3p0-eIduPWNqJ105M6f1QzvTunj6rBHMrrzS7pixouJvlTnPmiMXi2hMu4TL9Uv-NK_uulWoMSxyC4rUeWqrl3STdNbXxiiqS_UIUorSe43uT3Q1su-TOiVgsJ6_zEwMD0K1S5jllOhw0bvvoA.jpg

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለስራ ፈጣሪዎች ያለማስያዣ ድጋፍ ሊያደርግ ነዉ ተባለ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀሳብ ያላቸዉ ሀሳባቸዉ ተወዳዳሪ ሆኖ ላሸነፍ እና ወደምርት ቢገቡ አዋጪ ይሆናሉ ብሎ ላሰባቸዉ ስራ ፈጣሪዎች፣ ያለማስያዣ ድጋፍ ለማድረግ ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር መስማማቱ ተገልጿል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት፣የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት በርካታ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከልማት ባንክ ጋር የተደረገዉ ስምምነትም ለስራ ፈጣሪዎቾ አበረታች ነዉ ብለዋል።

ተቋማቸዉ ሌሎች መንገዶችንም እየተመከተ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ንጉሱ፣ አሰራሮችን፣ፖሊሲዎችን እና ስትራቲጂዎችን በመቀየስ ላይ ይገኛል ብለውናል።
ሀገሪቱ የነበራትን የጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስትራቴጂ ለሶስተኛ ጊዜ የመከለስ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ሚኒስቴር ድኤታዉ።
ይሁን እንጂ ስትራቴጂዉ ወደ ፖሊሲነት ማደግ ስላለበት በፖሊሲ ደረጃ ተቀርፆ፣ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ይላካል መባሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply