የኢትዮጵያ ሕዋ ሳይንስ ኢንስቲትዩት በቻይና መንግሥት ድጋፍ የሌሎች አገራትንና ድርጅቶችን የሳተላይት መረጃ የሚቀበልበት ጣቢያ ማቋቋሙን የቻይናው ዥንዋ ዘግቧል።

ተቋሙ፣ የሌሎች አገራትንና ድርጅቶችን የሳተላይት መረጃዎች በመቀበል፣ በማቀነባበርና በመተንተን ገቢ ማግኘት መጀመሩን መግለጡን ዘገባው አመልክቷል።

የመረጃ መቀበያ፣ ማቀነባበሪያና መተንተኛ ጣቢያው የተተከለው እንጦጦ ተራራ ላይ ነው።

የጣቢያው አገልግሎት ተጠቃሚዎች፣ በበጀትና ሌሎች እጥረቶች ሳቢያ ምድር ላይ የሳተላይት መረጃ መቀበያና የምርምር ጣቢያ የሌላቸው አገሮችና ድርጅቶች እንደኾኑ ኢንስቲትዩቱ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።

ባኹኑ ወቅት ጣቢያውን የሚመሩት ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች እንደኾኑ ተገልጧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply