“የኢትዮጵያ ሕዝብ የቱ ነው?” – ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ

(ሸክም የበዛበት ትውልድ፡2009 እና የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ)

በኹለንተናዊ የማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የዓለምም ኾነ የሀገራችን ትንታኔዎች ውስጥ ሕዝብ የሚለው ቃል እጅግ ተዘውትረው ከሚነሱ ቃላት መሐከል ዋነኛውና የኹሉ ነገር ማጠንጠኛ ኾኖ እናገኘዋለን፡፡

እንግሊዘኛው መዝገበ ቃላት ሕዝብ (people) ማለት”The members of a particular nation, community, or ethnic group” በማለት ሲፈታውwikipdia ደግሞ: “a people is a plurality of persons considered as a whole, as is the case with an ethnic group or nation.” በማለት ያስቀምጠዋል፡፡

በዘመናችን ከሕዝብ ጋር ተያይዞ እጅግ ወሳኝ ከኾኑ ጽንሰ ሀሳቦች መሐከል አንዱ ዲሞክራሲ ነው፡፡ Democracy (Wikipedia): ‘Literally ‘rule of the people’’ በማለት ሲገልጽ ይህን ታላቅ ጽንሰ ሀሳብና ተግባር ከመተንተን አንጻር እጅግ ጎልተው ከሚነሱ ታላላቅ ጥቅሶች (quotes) መሐከል አንዱና ዋነኛው የአሜሪካው ፕሬዝደንት አብርሃም ሊንከን (1809 – 1865) ፡ ዲሞክራሲን፡ ‘Government of the people, by the people, for the people’ ሲሉ የገለጹትን እናገኛለን፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ እጅግ በተደጋጋሚ በታሪክም ኾነ ዛሬ በምንኖርበት ዓለም ኾነ ሀገር “ሕዝብ ኃያል ነው”፤“ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው”፤“ያለ ሕዝብ ፈቃድ”፤“ሕዝብ ያላመነበት”፤ – – – ወዘተ ተብሎ በተለያየ አውድ ለተለያዩ ዓላማዎችና ትንታኔዎች ይጠቀሳል፡፡ እንዲህ የሚገለጸው “የትኛው የዓለም በተለይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው?

ይሄበምሁራን፣ በገዥዎች፣ በመሪዎች፣ በባለሙያዎች፣ በሰባኪዎች፣ በጸሐፍቶች፣ በጋዜጠኞች፣በታጋዮች፣ በአታጋዮች፣ በአዋቂዎች፣ በታዋቂዎች፣ አዋቂና ታዋቂ ነን በሚሉ – – – ወዘተ በመደበኛ (formal)የሚድያ ቃለ መጠይቆችና መርሐ ግብሮች፣ የአደባባይ ንግግሮች፣ የመድረክ፣ የስብሰባ (ሕዝባዊና የበርካታ ሰዎች ስብስብ ውስጥ)፣ የጉባኤ፣ የምክር ቤት፣ የጽሑፍ ሥራዎች፣ መፈክሮች፣ መግለጫዎችና ደብዳቤዎች፣ የፕሮፕጋንዳ ሥራዎች- – – ወዘተላይ በእጅጉ ‘በሳል’፣ ‘አዋቂ’፣ ‘ሥልጡን’፣ ‘ሃይማኖተኛ’፣ ‘የዋህ’፣ ‘ቆራጥ’፣ ‘ጀግና’፣ ‘እውነተኛ’፣ ‘ቁም ነገረኛ’፣ ‘ማንንም የማይፈራ’፣ ‘ታጋሽ’፣ ‘ጨዋ’፣ ‘ታሪክ ሰሪ’ – – – ወዘተ ተብሎ የሚወደሰው እና በእጅጉ ከፍ ከፍ የሚደረገው፤

ነገር ግን መደበኛ ባልሆኑ (informal) መድረኮች፣ የወዳጅ ውይይቶችና ጭውውቶች፣ የጓዳ ስብሰባዎች (የውስጥ ስብሰባ ላይ)፣ በምክንያታዊና በጥልቅ ጥናት ገለጻ ላይ፣ በሀሳብ የውይይት ልውውጥ፣ በብስጭት ወቅት፣ በመጠጥ፣ በልብ ለልብ ግልጽ የዕይታ ትንታኔዎች – – – ላይ ደግሞ እንዲሁ በተመሳሳይ በነዚያ አዋቂና ታዋቂ ነን በሚሉ፣ አዋቂዎች፣ ታዋቂዎች፣ አታጋዮች፣ ታጋዮች፣ ጋዜጠኞች፣ ጸሐፍቶች፣ ሰባኪዎች፣ ባለሙያዎች፣ መሪዎች፣ ገዥዎች፣ ምሁራን – – – ወዘተእጅጉን ‘አላዋቂ’፣ ‘ከነፈሰው ጋር የሚነፍስ’፣ ‘ዝቅተኛ የማስታወስ ችሎታ ያለው’ (short memory)፣ ‘አስመሳይ’፣ ‘ያልሠለጠነ’፣ ‘እንደመሩት የሚኾን’፣ ‘በስሜት የሚመራ’፣ ‘ፈሪ’፣ ‘አጨብጫቢ’፣ ‘አሽቃባጭ’፣ ‘መዝናናት እንጂ ቁም ነገር የማይወድ’፣ ‘ንቃተ ህሊናው ዝቅተኛ የኾነ’፣ ‘ዘወትር የሚመራ’፣ ‘በትንሽ ነገር የሚረካ’፣ ‘ጠላቱንና ወዳጁን የማያውቅ’፣ ‘ታሪክ ከመስራት ይልቅ በማውራት የሚኖር’፣ ‘ነገሮችን ቶሎ የማይረዳ’፣ ‘ከአዋቂ ይልቅ ታዋቂን የሚከተል’፣ ‘ተንኮለኛ, ቂመኛና ድብቅ’፣ ‘ቲፎዞ እንጂ ተጫዋች ያልኾነ/ የማይኾን’፣ ‘የተባለውን ሳያላምጥ የሚውጥ/የሚቀበል’፣ –  – – ወዘተ ተብሎ በእጅጉ የሚብጠለጠለው ያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው፡፡

በየትኛውም ጽንሰ ሀሳባዊ ዕሳቤም ኾነ ዕሳቢያዊ ትንታኔ ሁለት ተቃራኒ የኾኑ ነገሮች በተመሳሳይ አካል፣ ኹኔታ፣ ወቅትና ጊዜ ላይ ተመሳሳይ ሊኾን አይችልም፡፡ ለአብነት፡- አንድ ሰው (ሕዝብም ሊኾን ይችላል፡፡) ሃይማኖተኛ ተብሎ ሃሰተኛ፤ አዋቂ ተብሎ አላዋቂ፣ ግልጽ ተብሎ አስመሳይ – – – ወዘተ ሊኾንአይችልም፡፡

ነገር ግን አንድ ሰው አንዴ ሃይማኖተኛ ሌላ ጊዜ ሃይማኖት የሌለው፤ በአንድ ነገር እውነተኛ በሌላው ሃሰተኛ፣ በአንድ ወቅት የሚያውቅ – ሌላ ጊዜ የማያውቅ፣ ለአንዱ ግልጽ ለሌላው አስመሳይ – – – ሊኾን ይችላል፡፡ ይህም በአካሉ፣ በኹኔታ፣ በወቅትና ጊዜ መለዋወጥና መደበላለቅ በእጅጉ ይኖራል፡፡ ፍጹም ተቃራኒ የኾኑ ባህሪያትና ጠባያትን ግን በተመሳሳይ አካል፣ ኹኔታ፣ ጊዜና ወቅት ላይ ከተገኘ ከኹለት አንዱ እንጂ ኹለቱም ፈጽመው እውነት ሊኾኑ አይችሉም፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ በሌላኛው ዐውድ ሕዝብ የሚለውን ቃል ሳይጠቀሙ አንዳች ኹለንተናዊ ሀገራዊ ጉዳይ ማንሣትም ኾነ መስበክ እጅግ አስቸጋሪ ብሎም ረቀቅ ካደረግነው የማይቻል (impossible) ይኾናል፡፡

በዚህ ዐውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ የቱ ነው?

 1. በዕድሜ
 • ሕዝብ = ህጻን + ታዳጊ + ወጣት + ጎልማሳ + አዛውንት

በዚህ ውስጥ በሀገሩ ጉዳይ ወሳኝ ሚና ሊጫወት የሚችለው ወጣቱ፣ ጎልማሳውና አዛውንቱ ነው፡፡ ወጣቱ በብዙ ሀገራት ለሀገሩ ከመግለጫ ማጣፈጫነት ከመጠቀስ በዘለለ በሀገሩ ጉዳይ ወሳኝ አካል እንዳልሆነ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡

በዚህ ስሌት ሕዝብ = ጎልማሳ + አዛውንት ይኾናል፡፡ አብዝሃው ተገሎ ሳለ ሕዝብ የቱ ነው? ያ በየመድረኩና ሚድያው የሚወደሰው – ዲስኩር የሚቆረቆርለት ሕዝብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የቱ ነው?

 1. በትምህርት
 • ሕዝብ = ያልተማረው + በመማር ላይ ያለው + የተማረው

ኃያልና ተጽዕኖ ፈጣሪው የቱ ነው?ምሁሩ (በተለይ elits) ሕዝብን በተወካይነት ካባ የሚያሽከረክር አይደለምን? የሱን ግልጽና ስውር ፍላጎት/ቶች የአብዝሃ ፍላጎት/ቶች በማስመሰል የሚያቀርብ አይደለምን?አብዝሃ ባልተማረበት፣ ከትምህርት ገበታ በራቀበት በመፈክርና በባለቤትነት በውሳኔ እንዳለ የሚገለጽ – በተግባር ግን የሌለን – ሕዝብ ማለት ይቻላልን?

 1. በመራጭነት
 • ሕዝብ = ምርጫ መምረጥ (የማይችል + የሚችል) ዜጋ

በአብዛኛው የዓለም ሀገራትም ኾነ በሀገራችን ምርጫ መምረጥ የማይችለው ቁጥር መምረጥ ከሚችለው እጅጉን በጣም ይበልጣል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ106 ሚሊዮን በላይ መኾኑን የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ መምረጥ የሚችለው ስንቱ ይኾን? በርግጠኝነት ምርጫ መምረጥ ከማይችለው እጅግ በጣም ያነሰ ነው፡፡ እንግዲህ አነስተኛው በአብዝሃ ላይ ይወስናል፡፡ አነስተኛው አብዝሃን በውስጠ ታዋቂነት ይገዛል፡፡ ይመራል፡፡

ለወሬ ማጣፈጫ፣ ለንግግር ማሳመሪያ፣ ለመድረክ ማድመቂያ፣ መባል ስላለበት – – – “ሕዝብ ኃያል ነው!”፤”ያለ ሕዝብ ፈቃድ ምንም ማድረግ አይቻልም!!!”፤”ሕዝብ ያልተሳተፈበት የትም አይደርስም!!!” – – – ትላንት ከትላንት ወዲያ ሲባል ነበር፡፡ ትላንት ሲባል እንደነበር ኹሉ ዛሬም ይባላል፡፡ ነገም ቢኾን መባሉ አይቀርም፡፡ የቱ ሕዝብ?የትኛው ሕዝብ?ምን የሚያደርገው? ተብሎ ግን ትርጉም ባለው መንገድ አይጠየቅም፡፡አይመረመርም፡፡አይስተዋልም፡፡ አይተነተንም፡፡

 1. በንቃተ ህሊና
 • ሕዝብ = ንቃተ ህሊናው (ዝቅተኛ + መካከለኛ + ከፍተኛ)
 • ሕዝብ = ስለሀገሩ ወቅታዊ ኹኔታ መረጃና ማስረጃ(የሌለው +ያለው)

ሕዝብ ማለት ስለሀገሩ የትላንትና የዛሬ ኹለንተናዊ መረጃና ማስረጃ ያለው እና የሌለው ዜጋ ድምር ነው፡፡ ኹለቱም ወሳኝ አካላት ናቸውን?እንዴት አብረው በጋራ ጉዳይ ላይ አብረው መቆም ይችላሉ? ኃያሉና ተጽዕኖ ፈጣሪውስ የትኛውነው? ጥቂቱ ወይስ አብዝሃው?

 1. በውሳኔ ሰጪነት
 • ሕዝብ = በውሳኔ ሰጪነት ሂደት (የማይሳተፍ + የሚሳተፍ)
 • ሕዝብ = በውሳኔ ሰጪነት ሂደት(ያልተወከለ + የተወከለ)

የኢትዮጵያ ሕዝብ በውሳኔ ሰጪነት ሂደት የሚሳተፈውም ኾነ የማይሳተፈው አልያም የተወከለውና ያልተወከለው ድምር ነው፡፡ ስለኾነም በኹለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚሳተፈውና የተወከለው – ከማይሳተፈውና ካልተወከለው እጅጉን በላቀ ደረጃ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡ ሕዝብ ማለት ግን የሁለቱ ድምር ነው፡፡ ‘የኢትዮጵያ ሕዝብ ወሳኝ ነው’ ሲባል በጽንሰ ሀሳብም ኾነ በተግባር የሚያመለክተው ጠቅላላውን ሕዝብ ሳይኾን ጥቂቱን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ = በውሳኔ ሰጪነት ሂደት እና የኢትዮጵያ ሕዝብ = በውሳኔ ሰጪነት ሂደት የተወከለው ማለት ነው፡፡ የማይሳተፈውና ያልተወከለው አብዝሃ እን£ ቢኾን ቤት አድርጎ ወሳኝ ይኾናል?

 1. በአ‘‘
 • ሕዝብ = በገጠር የሚኖረው + በከተማ የሚኖረው

የሀገራችን ሕዝብ በአብዝሃ ከ80 በመቶ በላይ የሚኾነውበገጠር የሚኖር ነው፡፡ የሀገሪቱ ገዥዎች፣ ምሁራንና መሪዎች የሚኖሩት በከተማ ነው፡፡ ወሳኝ የመንግሥት ኹለንተናዊ አካላት የሚገኙት በከተማ ነው፡፡ የሀገሪቱን የዛሬና የነገ እጣ ፋንታ በውሳኔያቸው የሚያሽከረክሩትም ኹለንተናዊ ተuማት በከተማ ያሉት ናቸው፡፡

ከተማዊ የአ‘‘ር ዘይቤ ያላቸው ጥቂቶች ገጠራዊ የአ‘‘ር ዘይቤ ያላቸውን አብዝሃዎች፤ ከተማዊ አስተሳሰብና አመለካከት ብሎም ፍላጎት ያላቸው ጥቂቶች ገጠራዊ አስተሳሰብና አመለካከት ብሎም ፍላጎት ያለቸውን አብዝሃዎች፤ ከተማዊ እምነት, እውቀትና ድርጊት ያላቸው ጥቂቶች ገጠራዊ እምነት, እውቀትና ድርጊት ያላቸው አብዝሃዎችን ይገዛሉ፡፡ ይመራሉ፡፡

እነሱ አናሳ ኾነው ሳለ በአብዝሃ ላይ ይወስናሉ፡፡ አብዝሃ ላይ ይፈርዳሉ፡፡ አብዝሃን ያስገዛሉ፡፡ያስመራሉ፡፡’ሕዝብ የወደደውና የፈቀደው’ ብለው ያነበንባሉ፡፡ በጽንሰ ሀሳብ ሕዝብ የሁለቱ በገጠርና በከተማ የሚኖር ዜጋ ድምር መኾኑን አስቀምጠው በግብር – በድርጊት ትርጉም ባለው መንገድ ካለው ተጽዕኖና ኃይል አንጻር ስንመረምር፡

 • ሕዝብ = በከተማ የሚኖረው ኾኖ እናገኘዋለን፡፡

በሌላ በኩል በአ‘‘ር

 • ሕዝብ = ዝቅተኛው ዜጋ + መካከለኛው ዜጋ +ሀብታሙ ዜጋ

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ (ከዝቅተኛም እጅግ ዝቅተኛ) ላይ ያለ ሲኾን ከሀብታሙ ዜጋ እጅጉን የበለጠ ከዝቅተኛው ዜጋ ደግሞ በአንጻሩ እጅጉን በጣም ያነሰው ደግሞ መካከለኛው ኾኖ እናገኘዋለን፡፡

በወሳኝ ኹለንተናዊ የሀገር ጉዳዮች ላይ ወሳኝ ድርሻ ያላቸው ሀብታሞቹና መካከለኞቹ ናቸው፡፡ ዝቅተኞቹ ግን በምርጫ ወቅት ካልኾነ በሌላ ጊዜ ተፈላጊነታቸው ምን እንደኾነ ለቀባሪው ማርዳት ነውና እንለፈው!!!

ማንኛውም ሥርዓተ መንግሥት ድሃ አይወድም – ባለገንዘብ ይወዳል፡፡ ከምላሱ ባሻገር በልቡ ድሃ የሚወድ መንግሥት እድሜው አጭር ነው፡፡ አብዛኞቹ መንግሥታት ባለሀብት ወዳጅና አፍቃሪ እጅግ – እጅጉን ስናረቀው አምላኪም ጭምር ናቸው፡፡

ከላይ እንደጠቀስነው English Oxford Living Dictionaries: ሕዝብ፡- “Human beings in general or considered collectively” በማለት በሌላ በኩል ሕዝብን ከሕዝባዊነት ጋር ሲያስተሳስር ወደ ታችኛው የሕብረተሰብ ክፍል አውርዶ “A person who comes from an ordinary background or identifies with ordinary people“ሲል ብያኔ ይሰጠዋል፡፡

ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ፡ ሰዋሰው፡ ወግስ፡ ወመዝገበ፡ ቃላት ሐዲስ እንዲሁ ሕዝብ “በቁሙ፡ ወገን፡ ነገድ፡ የተሰበሰበ፡ ብዙ ሰው፤ ጉባኤ፡ ሸንጎ፤ ልቅሶኛ፡ ሰርገኛ፡ ገበያተኛ፡፡ ያንዲት አገር፡ ያንዲት ከተማ ወይም ያንድ ብሔር፡ ያንድ መንግሥት፡ ሰው uንuውና ሕጉ አንድ የኾነ፡ ባንድ ሕግ የሚኖር፡፡ ውስጠ፡ ብዙነት፡ ስላለው፡ ባንድም፡ በብዙም፡ በወንድም፡ በሴትም ይነገራል፡፡” በማለት ሕዝባዊን ደግሞ “በቁሙ፡ የሕዝብ፡ ወገን፡ ካህን፡ ያይደለ፡ ማይምን፡ ጨዋ ባላገር” ብለው አስቀምጠውታል፡፡ ታድያ በጽንሰ ሀሳብና በተግባር ያለው ኃያሉና ተጽዕኖ ፈጣሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ የቱ ነው?

 1. በታሪክ
 • ሕዝብ = ታሪክ ተመልካች + የታሪክ ስራ አደናቃፊ + ታሪክ ሰሪው
 • ሕዝብ = በታሪክ ፍጻሜ የሚኮራ + ታሪክ ፈጻሚ

ከታሪክ አንጻር የሰው ልጅን ኹለንተናዊ የለውጥ ሂደት ስንመለከት ጥቂቶች አብዝሃን ያስከተሉበትን እንጂ አብዝሃ ጥቂቶችን የመሩበትን ፍጻሜ ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ጥቂቶች ናቸው ለመልካምም ኾነ መልካም ላልኾኑና ለሚባሉ ክስተቶች ግንባር ቀደም ተዋንያን ሊኾኑ የቻሉት፡፡ ከዚህ ተነሥተን ዛሬም ኾነ ነገ ከዚህ የተለየ ነገር ሊኖር አይችልም ማለት ይቻል ይኾን?

ኹሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተመሳሳይ ደረጃ ንቁ፣ አዋቂና ቆራጥ ሊኾን አይችልም፡፡ ኹሉም በአንድ ጊዜ ተመሳሳይ ነገር ሊያምን – ሊያስብ – ሊያውቅ – ሊያደርግ – ሊተጋ – ዋጋ ሊከፍል፤ በተመሳሳይ ኹኔታ፣ ጊዜና ወቅት ሊነሣ አይችልም፡፡ ጥቂቶች ተነሥተው ወደ አብዝሃ ያድጋሉ እንጂ አብዝሃዎች ጥቂቶችን ሊያነሱ አይችሉም፡፡ በሂደት ግን አብዝሃዎች ጥቂቶች ይኾናሉ፡፡ ጥቂቶችንም ይጫናሉ፡፡ ረቀቅ ሲል በማይታይ እጃቸው (invisible hands) ይረግጣሉ፡ ይረጋግጣሉ፡፡ ያስረግጣሉ፡፡ ለዚህም ከአብዘሃ የተለየ ሀሳብና ድርጊት – በማሰባቸውና በመፈጸማቸው ታላቅ ቅጣትን የተቀጡ ፈላስፋዎች፣ መምህራን፣ ተመራማሪዎች፣ ጸሐፍቶች፣ ገዥዎችና መሪዎች – – – ታሪካቸው ህያው ምስክር ነው፡፡ በዚህም ለውጥ ከጥቂቶች ወደ አብዝሃ በመሪነት የሚሸጋገር፤ በሂደት በአብዝሃ የሚጠበቅ ውጤት ነው፡፡

ታሪክ በባህሪው በጥቂቶች ተሰርቶ በጠባይ የብዙዎች ይደረጋል፡፡ ለዚህም ውክልናና ባለቤትነት የተሰኙ ጽንሰ ሀሳቦች መጠቀሚያና መሸፈኛ ይኾናሉ፡፡

ከላይ የተጠቀሱት 7 ነጥቦች እርስ በራስ እጅጉን የተቆራኙና የማይነጣጠሉ በመኾናቸው አንዱን ከአንዱ ነጥሎ መመልከት እጅጉን ከባድ ነው፡፡ ሕዝብ፡ በኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚኖር የነጠላ ድምሮች ውጤት በመኾኑ የአብዝሃ መገለጫ አልያም መጠሪያ ነው፡፡

በመኾኑም በኹለንተናዊ ማለትም በማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳዮች ላይ ሕዝብ ይህን ማድረግ አለበት፤ ሕዝቡ ማመን፣ ማወቅ፣ ማድረግ፣ መንቃት፣ መታገል፣ መሞገት፣መሳተፍና ባለቤት መኾን አለበት – – – ወዘተ ስንል የቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ?የሚለውን ትርጉም ባለው መንገድ መመለስ ይኖርብናል፡፡

የዚህ ጥያቄ መመለስ ለተሻለ ኹለንተናዊ ተግባቦት ይጠቅማል፡፡ አለበለዚያ የንግግር ማሳመሪያ፣ የቃላት ማጣፈጫ፣ አማራጭ ከማጣት፣ ከግንዛቤ እጥረት፣ ከተለምዶ – ከሴራ አንጻር – – – የሚባል ሲኾን ጊዜ ማባከኛ፣ ገጽ መሙያ፣ ስራ መፍቺያ/መፍጠሪያ፣ የአየር ሰአት ከመያዝ፣ ከፕሮፕጋንዳ ጋጋታነት የዘለለ ፋይዳ ሳይኖረው ያልፋል፡፡

ስለኾነም በመደበኛም (formal) ኾነ ኢ-መደበኛ በኾኑ (informal) ኹለንተናዊ መንገዶችና ግንኙነቶች ኃያልና ተጽዕኖ ፈጣሪ ተብሎ የተጠቀሰው፣ የሚጠቀሰውና ሊጠቀስ የሚገባው የቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው?ብሎ መመርመርና ማስተዋል የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ፈጣሪ ሀገራችን ነጻ ፍቃድንየኹሉ ነገር ማዕከል ወደሚያደርግ የዕሳቤ ሂደት ትገባ ዘንድ ይርዳን!

ቸር እንሰንብት!  

የ17 ቀኑ ተከታታይ ድራማ

ያው ሁላችሁም እንደምታውቁት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 17 ቀን ተገማግሞ ባለ ስምንት ገጽ ስክሪፕት ጽፎ ነበር።

ይኼ ባለ ስምንት ገጽ ስክሪፕት በሦስት ክፍል ተዘጋጅቶ በአራት ገጸባህርያት ተተውኖ ለሕዝብ ዕይታ የበቃው ደግሞ ባለፈ ሰሞን ነበር። አቶ ደብረጺዮን ገብረሚካዔል – “ጥገኞችን መምታት” የሚል አዲስ ስያሜ ደጋግሞ በማንሳት፤ አቶ ኀይለማርያም ደሳለኝ – የአቶ ደብረጺዮንን “የጥገኞች ትንተና” በማስተጋባት፤ አቶ ደመቀ መኮንንም በተመሳሳይ “የጥገኞችን” አዲስ ዜማ በካድሬያዊ ከበሮ በመደለቅና አቶ ለማ መገርሳ “ጥገኛ” የምትለዋን የሕወሓት ስያሜ ላለመጠቀም በመጠንቀቅ በተከፈለ ልብ ኾነው ትወናቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቅርበዋል። የፈረደበት የኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ የፖለቲካ ተከታታይ ፊልም ተለቆበታል።

የፊልሙ ርዕስ ለብዙ ኢትዮጵያውያን አዲስ አይደለም፤ “ጥልቅ ተሃድሶ” ይባላል። ይኼ ድራማ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሃይማኖታዊ ሥነ ልቡና በመኮርኮር “ማሩኝ ይቅር በሉኝ”ን እጅ መንሻ አድርጎ – በሕዝቡ አንጀቱ ውስጥ እንደ ቄጤማ በመጎዝጎዝ ላይ ያተኮረ ነው። ጭብጡ የሚያጠንጥነው – ዲሞክራሲውን በማስፋት፣ ማዕከላዊን በመዝጋት፣ “አንዳንድ” የፖለቲካ አመራሮችን በመፍታት፣ የፍትህ ሥርዐቱን በመፈተሽ፣ የትግራይ/የሕወሃት የበላይነት አለመኖሩን በመለፈፍና የቋንቋ ፌዴራልዚሙንና ሕገ-መንግሥቱን እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አይነኬ አድርጎ በማሳየት ነው። ከዚያም በተጨማሪ እንደማንኛውም ተከታታይ ፊልም ጡዘቱን ከፍ ማድረግ ተገቢ በመኾኑ በግንባሩ ድርጅቶች መካከል መቋሰል፤ መጠራጠርና አለመተማመን መንግሡን ተዋንያኑ ይተርኩልናል።

የድራማው አጠቃላይ ይዘትና ዓላማ – የኢትዮጵያን ሕልውና መታደግና እውነተኛ የኾነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት መፍጠር ሳይኾን – ኢሕአዴግን ከገባበት ወጥመድ ውስጥ ለማውጣት “የፖለቲካ ስብከት” አዘጋጅቶ መቅረብ ነው ብዬ ነው የማስበው። ግንባሩ በሕዝብ ያጣውን አመኔታ መልሶ ለማግኘት “ችግሩ የሥራ አስፈጻሚው ነው” በሚል “የይቅርታ አድርጉልኝ” ስብከት – የሕዝብ እምቢተኝነት ናዳውን ለማምለጥ የመሞከር አዝማሚያም የስክሪፕቱ ዋና አካል ነበር። ድራማው ካስቀመጠው ግብ አንዱ ፓርቲውን ከገባበት አዘቅት ለማውጣት ያለው ብቸኛ አማራጭ “ራስን ተጠያቂ” አድርጎ ማቅረብ ነው የሚለው ነው። ኢሕአዴግ ለዓመታት ሲዘምረው የቆየውን “የጸረ ሰላም ኀይሎች ትርክት” ሰርዞ “ኢሕአዴግ አምላክ አይደለም” በሚል ፖለቲካዊ የማደንዘዣ መርፌ – የታመመውን ፖለቲካ ለመውጋት ሽር ጉድ በማለት ላይ እንደሚገኝም በዚህ ድራማ አሳይቶናል።

ሁሉም ተዋንያን “ዲሞክራሲውን ማስፋት” በሚለው ጉዳይ ላይ የየራሳቸውን አስተያየት ሰጥተዋል። ይህ አባባል በመሠረቱ ትክክለኛ አባባል ነው ወይ ብሎ መጠይቅ ያስፈልጋል። ኢሕአዴግ በሕገ መንግሥቱ የሰፈሩት የግለስብም ኾነ የቡድን ዴሞክራሲያዊ መብቶች የማይጣሱ፣ የማይገሰሱና፣ የማይሸራረፉ ኾነው ሳለ፤ “ማስፋትና ማጥበብ” በሚል የቃላት ጫዎታ ሸንጋይ ኾነው ለማምለጥ እየሞከሩ ይገኛሉ። የጨዋታ ሕጉን ያስቀመጥነው እኛ ስለኾንን – ዲሞክራሲውን ለማስፋት ተዘጋጅተናል በሚል አሁንም ሕዝብን ቁልቁል ከማየትና ከመመልከት አለመውጣታቸውን እያረዱን ነው። “ሰጪና ነሺ ነኝ” ከሚለው አምባገነናዊ ባሕርያቸው ሳይፈወሱ “በጥልቅ ታድሻለሁ” በሚል ዜማ ሕዝቡን ለማጃጃል መሞከር – ግራም ነፈሰ ቀኝ ነጻነትና እኩልነት ከጠማው ሕዝብ ጋራ መልሶ የመጋጨትን በር ወለል አድርጎ መክፈት ነው።

ዲሞክራሲ ማለት “ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት የሚኾንበት” ወይም ደግሞ “ሕዝብ ወኪሎቼ የሚላቸውን ሰዎች የፖለቲካ ልብሰ ተክህኖ አልብሶ ጥቅሙን ለማስጠበቅ የሚተዳደርበት ሥርዐት ማለት ነው። ስለዚህ ዲሞክራሲ አንድ ፓርቲ የሕልውና አደጋ ውስጥ በገባ ቁጥር የሚያሰፋውና የሚያጠበው ጥብቆ አይደለም።

በድራማው ከተነሱት ሐሳቦች አንዱ ለዘመናት ዜጎቻችን ሲኮላሹበት የነበረውን ማዕከላዊን መዝጋትና ሙዚየም ማደረግ የሚለውና ከሰብአዊ መብጥ ጥሰት ጋራ ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው የፍትህ ሥርዐት ጉዳይ ነው። ይህን ጉዳይ በተመለከተ አቶ ለማ መገርሳ በተለያዩ መድረኮች ላይ ካሳዩት ልበ ሙሉነት ላላ ባለ መንገድ እንዲህ ሲሉ አቅርበውታል፦

“በተለይም የሰብአዊ መብት ጉዳይ፤ የማዕከላዊ ምርምራ ለረዥም ዘመናት ዜጎቻችን ሲኮላሹ የነበረበት ቤት እንዲዘጋ መወሰኑ አንድ ጉዳይ ኾኖ፤ አጠቃላይ የፍትህ ሥርዐቱንም ማየቱ አስፈላጊ እንደኾነም ታይቷል። ፍትህን በማስፈን ረገድ የፍትህ ሥርዐታችን ለውጦች ያሉበት ቢኾንም፤ የተጠበቀውን ያህል፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና እየጎለበተ እንደመሄድ፤ አሁንም ጭምር ብዙ ሮሮርና ስሞታ ከሚሰማባቸው ዘርፎች አንዱ የፍትህ ሴክተሩ/ የፍትህ ዘርፉ ነው።”

በርግጥ አቶ ለማ እንደጓዳቸው እንደ አቶ ኃይለማርያም ማዕከላዊን በተመለከተ “ደርግ” ላይ አለመንጠልጠላቸው ደግ ነገር ነው። ጉዳዩን “ዜጎቻችን የሚኮላሹበት” በሚል ማስቀመጣቸውም ተገቢና ትክክለኛ ነው። እግረመንገዳቸውን ዜጎቻችን አሁንም እየተኮላሹበት እንደኾነ በገደምዳሜ እየነገሩን ስለኾነ። ነገር ግን “ፍትህን በማስፈን ረገድ የፍትህ ሥርዐታችን ለውጦች ያሉበት ቢኾንም” የሚለው አባባላቸው በሕዝብ ዘንድ እያተረፉ ለመጡት ተቀባይነት ራሱን የቻለ ትልቅ ደንቃራ የሚኾንባቸው ይመስለኛል። አቶ ለማ ባንድ በኩል “እጃችን ላይ ደም አለ” እያሉ እየነገሩን በሌላ በኩል ደግሞ “የፍትህ ሥርዐቱ ለውጦች ታይተውበታል” ብለው ያደናግሩናል። አሁን ጥያቄ የሚኾነው – እንደ አቶ ለማ ያለ እውነትን ለመጋፈጥ በዚህ ደረጃ ለመጓዝ ፈቃድ እያሳየ ያለ ሰው – በፍትህ ሥርዐቱ ውስጥ ታየ የሚባለውን ለውጥ “ከደሙ ንጹሕ ኾኖ” ማሳየት የሚችለው በእንዴት ያለ አኳኋን ነው የሚለው ነው።

የፍትህ ሥርዐቱ ሰለባ የኾኑት የፖለቲካ እስረኞች የአገሪቱን እስር ቤት ባጣበቡበት፤ የእስር ቤት አስተዳዳሪዎች ለዳኞች በማይታዘዙበት፣ እርስዎ – ራስዎ ለመከላከያ ምስክርነት ተጠርተው “በሥራ ይበዛብኛል” ሰበብ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በቀሩበት፣ “እጃችን ላይ ደም አለ” የሚል ግልጽ የኾነ የእምነት ክህደት ቃል የሰጡት እርስዎ በሕግ በማይጠየቁበት፣ በተቃራኒው ሐሳባቸውን በጽሑፍና በንግግር በማቅረባቸው ብቻ “አሸባሪዎችና ሕገ መንግሥት የናዱ” ተብለው በሚሰቃዩበት አገር ላይ “የፍትህ ሥርዐቱ ለውጥ እየታየበት ያለ ቢኾንም” ብሎ ማውራት በየቀኑና በየሰዓቱ ያለጥፋታቸው በተጋዙት ዜጎቻችን ላይ መሳለቅ ይመስለኛል።

ሌላኛው በድራማው ላይ የተነሳው ጉዳይ “የሕወሃት/ትግራይ የበላይነት” አለ ወይስ የለም የሚለው ነው። እውነት ለመናገር ይህን ጉዳይ እንደማንሳት የሚቀፈኝና የሚጎመዝዝኝ ነገር የለም። ነገሩ የሚቀፈኝ ያለውን ሐቅ ለመናገር ድፍረት አጥቼ ሳይኾን – በአንድም ይኹን በሌላ መንገድ የዘውጌና የጎሰኝነት ፖለቲካ ጭቃ አቡኪ ከመኾን የዘለለ አንዳችም ትርፍ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ያመጣል ብዬ ስለማላስብ ነው። የዘውጌ ፖለቲካ አውሮፓውያንን ከልክ ያለፈ ዋጋ አስከፍሏቸዋል። በ10 ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ቀርጥፎ የበላው የዘውጌ ፖለቲካ ሰበብ ነው።

የኾነው ኾኖ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አይተገበርም የሚለው ተቃውሞ ለብዙዎች ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት በኾነ በማግሥቱ – ያሰቡትና የፈለጉት ያልተሳካላቸው የሕወሓት ጎምቱዎች ይቺኑ “የትግራይ የበላይነት” የምትል አጀንዳ ይዘው በፋና ስቱዲዮ መሽገው ነበር። አቶ አባይ ጸሐዬ፣ አቶ ስዩም መስፍንና አቶ ደብረጺዮን ገብረሚካዔል አጀንዳውን ሲጋገሩ ነበር። ሕወሓት ሕልውናውን የሚፈታተን ጉዳይ በገጠመው ቁጥር ይቺኑ “የትግራይ የበላይነት” የምትባል ጆከሩን ይመዛታል።

በማግስቱ ደግሞ ኢታ.ር ሳሞራ የኑስ የትግራይ ወጣቶችን ሰብስቦ “ሕወሓት ማለት ትግራይ ነው፤ ትግራይም ሕወሓት” ብሎ በአደባባይ ተናገረ። ኢታማጆሩ የረሱት አንድ ነገር ቢኖር በመርህ ደረጃ መከላከያው ከፖለቲካ የጸዳና ታማኝነቱ ለሕገ- መንግሥቱና ለሕዝቡ መኾኑን ነው። እንግዲህ ገለልተኛ መኾን የነበረበት የመከላከያ ኢታማዦር ሹም፤ በዚህ ደረጃ ዘው ብሎ “በነጻ ፈቃዱ የፈለገውን መምረጥ የሚችለውን የትግራይ ሕዝብና ሕወሓትን ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ አድርጎ” መሳል የፈለገው ለትግራይ ሕዝብ ስለሚቆረቆር ወይስ . . . ? ሕወሓት “የትግራይ የበላይነት” የሚለው አጀንዳ የአደባባይ ወሬ እንዲኾን የሚፈልግበት ዋነኛ ዓላማ የኢትዮጵያ (የትግራይ ህዝብ ) “ብቸኛ አዳኛቸው” እርሱ ብቻ እንደኾነ ለማሳየት ነው።

የአንድ አገር ፖለቲካና ኢኮኖሚ በጥቅም በተሳሰሩ ጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ቁጥጥር ስር ሲወድቅ – በአጠቃላይ መዋቅሩ ውስጥ አንዱ የበላይ ሌላው የበታች የሚኾንበት ምቹ ኹኔታ ይፈጠራል። ይህን ጉዳይ የበላይና የበታች በሚለው ከማስቀመጥ ይልቅ ጌታና ሎሌ በሚለው ብንወስደው የበለጠ ነገሩን ግልጽ የሚያደርገው ይመስለኛል። በሀብትና በሥልጣን ኮርቻው ላይ የተፈናጠጡ ሰዎች ጌቶች፤ በሀብቱና በሥልጣኑ ርካብ ላይ ለመንጠላጠል የሚነሱና የሚወድቁት ደግሞ ሎሌ ይኾናሉ። በኢሕአዴግ መዋቅር ውስጥ ቁልፍ የኾኑ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሥልጣኖች በሕወሓት ጥብቅ ቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ አሌ የማይባል ጉዳይ ነው።

ለምሳሌ፦ የአገሪቱን መከላከያ፣ የአገሪቱን ደህንነት፣ የአገሪቱን ቁልፍ የኢኮኖሚ መዘውር የተቆጣጠረው ሕወሃት ነው። የፍትህ መዋቅሩ የወደቀው በሕወሃት እጅ ነው። በቁልፍ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ዳኛ ኾኖ የሚፈርደው የሕወሓት ስውር እጅ ነው፤ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች በሕወሃት መዳፍ ስር ናቸው፤ አሳሪው በትግርኛ፣ ታሳሪዎች ደግሞ በኦሮምኛ፣ በአማርኛና በብዙ ሌሎች ቋንቋዎች ያወራሉ።

አገር ቤት ወዳለ አንድ ወዳጄ ጋ ደወልኩና “እንዲያው ይኼን የሕወሓት የበላይነት የሚባል ፌዝ እንዴት ታየዋለህ?” ብዬ ጠየቅኹት። 15 ሺሕ ማይል ርቀት ላይ ተቀምጬ – በኤንተርኔት ከቃረምኩት መረጃ ይልቅ መሬት ያለው ሰው የበለጠ የሚናገረው ይኖረዋል ብዬ ነው ጥያቄውን ጣል ያደረግኹት። ወዳጄ፦

“እኔ እሱን ለማረጋገጥ ሩቅ መሄድ አይጠበቅብኝም፤ ማታ ሶፋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ቴሌቪዥኔን ስከፍት በግልጽ በየቀኑ ዐየዋለሁ። ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ ከሚለቀቁት የቴሌቪዥን ዜናዎች ውስጥ 75 በመቶ ለዜናው ምንጭ ተደርገው የሚቀርቡት የሥራ ኀላፊዎች፣ ዳይሬክቶሬቶች፣ የክፍለ ከተማ አስተዳዳሪዎችና የቀበሌ ሥራስኪያጆች የሕወሓት ሰዎች መኾናቸውን እያየኹ “አገሩ የማነው?” ብዬ መጠየቅ ካልጀመርኹ ዐይኔንም ጆሮዬንም መካድ ጀመሬያለሁ ማለት ነው።” አለኝ።

የወዳጄ ንግግርና ገለጻ ዘጠኝ ዓመት ወደኋላ እንድመለስ አደረገኝ። በ2001 ዓ.ም የቀበሌ መታወቂያ ለማሳደስ እትብቴ ወደተቀበረባት ቀበሌ ሄጄ ነበር። ተወልጄ ያደግኹባትን ቀጨኔን – ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጠጉሯ አውቃታለሁ። ሸማኔ፣ ሸክለኛና አንጥረኛ ዘመዶቼን በቤት ቁጥር አውቃቸዋለሁ። “ማ ቢወልድ ማ?” ብላችኹ ብትጠይቁኝ እሰከ ሰባት ቤት ልነግራችኹ ሁሉ እችላለሁ። ተራዬ ደርሶ ወደ ሥራ አስኪያጁ ቢሮ ገባኹ። ወደ ውስጥ ስገባ የማውቀውን አንድ የቀበሌዬን እትብተኛ አገኛለኹ የሚል ጉጉት ነበረኝ። ግን አልኾነም።

ልጅ እግሩ ሰውዬ “ተቀመጥ” አለኝ፤ ተቀመጥኹ።

ለመጀመርያ ጊዜ ከሰፈሬ ለአንድ ዓመት ያህል ርቄ ስመለስ ቀበሌዬ አዲስ ሥራ አስኪያጅ ሹማ እንደጠበቀችኝ የተረዳኹት ጠረጴዛው ላይ “ጎሳዬ  ሽፈራው” የሚል ስም ባለቤት ከኾነው እንግዳ ፊት ጋራ ከተጋፈጥኹ በኋላ ነበር። አቶ ጎሳዬን የዚህ ሰፈር ሰው ነህ አይደለህም በዬ ልጥይቅ አልጠይቅ እያልኹ ከራሴ ጋራ ተሟገትኹና፤ ተውኹት፤ በኋላ አቶ ጎሳዬ ማነው የሚለውን ለማጣራት ስሞክር – በኢሕአዴግ ጽ/ቤት ስር ለቀጨኔ የተሾመላት የሕወሃት ካድሬ መኾኑን ተረዳኹ። አቶ ጎሳዬ አሁን የጉለሌ ክፍለ ከተማ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኾኗል።

አዲስ አበባ ላይ በአሁኑ ሰዓት ሕወሓት አዲስ አበቤውን የሚያስተዳድረው በሕዝብ በተመረጡ አካላት ሳይኾነ – ተጓዳኝ ኾኖ በተቀመጠው ከኢሕአዴግ ጽ/ቤት በሚመጣ የሕወሓት ሹመኛ ነው። በዚህ መዋቅር ውስጥ ተመድበው በእያንዳንዱ ቀበሌና ክፍለከተማ “አላልቅ ያለ ጉዳይ” የሚያስፈጽሙት የሕወሓት ሥራ አስኪያጆች ናቸው። ሎሌዎቹ ባለጉዳዩን እንዲሄድ የሚመክሩት ወደ እነዚህ ሰዎች ነው። ሕወሓት በመከላከያና በደህንነት ብቻ ሳይኾን በዚህ መልኩም የአዲስ አበባ ጌታና የባላይ ናት።

እንግዲህ ጎበዝ፣ የዚህ ሁሉ ውስብስብ ችግር መንስዔው ዜጎችን እንድናይና እንድንመለከት የተደረግንበት የዘውጌ ፊዴራሊዝም መነጽር ነው። ሊቃነ መናብርቱ ደግሞ በጋራ “የዘውጌ ፌዴራሊዝም የችግር ምንጭ ሳይኾን የመፍትሄ አማራጭ ይዞ የመጣ ነው” የሚል መከራከርያ ያቀርባሉ። “ብሔሮችና ብሔረሰቦች በጋራ ያጸደቁት የቃል ኪዳን ሰነድ ነው፤ ችግሩ ፌዴራሊዝሙ በአግባቡ አለመተርጎሙና ጥገኞች ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ አንደኛ፣ ሁለተኛና፣ ሦስተኛ ዜጋ እንዳለ አድርገው ለመሳል በመሞከራቸው የተፈጠረ ችግር ነው” ሲሉም ይሟገታሉ።

መከራከሪያውን እንደ አንድ ሐሳብ አክብሬ ወስጄ ጥያቄ አነሳለሁ። የ27 ዓመቱ የዘውጌ ፌዴራሊዝም ጉዞ ከግማሽ ሚልዮን በላይ የሚኾኑ ዜጎችን ለመፈናቀል፣ ሺሕዎችን ለሞት፣ ሺሕዎችን ለእስራት፣ መቶ ሺሕዎችን ለስደት፣ ሚልዮኖችን ለስጋትና ለተስፋ ቢስነት ከዳረገ – የመፍትሄ ምንጭነቱ ከወዴት አለ? በዘውግ የመፋጠጡ አደጋ እኮ በእግር ኳስ ደጋፊዎች ደረጃ ወርዶ እየተመለከትን ነው፤ ምናልባትም በዚሁ ከቀጠለ፤ “እግር ኳስ በዘውግ የመፋለሚያ አውድማ ኾኖ ሰላም እያደፈረሰ ስላስቸገረ በአዋጅ ተክልክሏል” የሚል ሕግ የምናይበት ቀን ሩቅ ላይኾን ይችላል።

እኔ በበኩሌ የብሔር ብሔረሰቦች ቃል ኪዳን ግለሰባዊና ከዘውግ አጥር በላይ የኾነውን ሰዋዊ ማንነቴን የሚጨፈልቅ ስለኾነ – በቃል ኪዳኑ አልስማማም። ከሰዋዊ ልዕልናዬ ጋራ ይጋጭብኛል። ቋንቋዬ የማንነቴ አንድ ሰበዝ እንጂ ምሉዕ የማንነት መገለጫዬ አይደለም። ቋንቋ ከማወቄ በፊት ሰው ነበርኹ፤ ባህል ከማወቄ በፊት ሰው ነበርኹ። አሁንም ሰው ነኝ። እነዚህ ሁለቱ እውቀቶች ስለ ልዩነት እንጂ ስለአንድነት የሚገልጡት አንዳችም ነገር የላቸውም። እኔን ከሌሎች ጋራ የሚያመሳስለኝና አንድ የሚያደርገኝ የሰው ልጅ ዝርያ መኾኔ ብቻ ነው። የሰው ልጅ በዘር አንድ ነው። ዘረኝነት የሚባለው ጽንሰ ሐሳብ የተወላገደና ያለቦታው የተደነጎረ – ከፋፋዮች ለሕዝብ ያቀበሉት የሐሰት ቃል ነው። ዘውገኝነትና ጎሰኝነትን ማጦዝን “ዘረኝነት” የሚል ለብስ አልብሰው የሚራኮቱ ሰዎች በድቡሽት ላይ የቆመ ሐሳብ ይዘው ነው የሚናውዙት። በተፈጥሮ ዑደት ውስጥ የሰው ልጅ ዘሩ አንድ ነው። ሰው መኾኑ ብቻ። ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 27 ዓመታት በተግባር የታየው በቋንቋና በባህል ቃለ መሃላ የተቧደኑ ኀይሎች ሰው መኾንን እያመከኑ መምጣታቸው ነው።

ባለፉት 27 ዓመታት የታዘብኩት ሌላኛው ነገር – “የሕግ የበላይነት” በሚባለው ቃል ላይ እየተደረገ ያለውን ከፍተኛ የኾነ መዘባበት ነው። እንዳለመታደል ኾኖ የሰው ልጅ ከእንስሳ የሚያንሰው [ልብ በሉ የሚያንሰው ነው ያልኹት] ያለ ሕግና ያለ ደንብ መኖር የማይችል አሳዛኝና ምስኪን ፍጡር በመኾኑ ነው።

እንስሳት የተጻፈ ሕግ የላቸውም፤ እንስሳት ዐሥርቱ ትዕዛዛት የላቸውም፣ እንስሳት ኮከብ ቆጣሪ የላቸውም፣ ነገር ግን ነገ ሊፈጠር የሚችለውን ተፈጥሯዊ አደጋ አስቀድመው የሚያውቁበት ተፈጥሮ የቸረቻቸው ደመ – ነፍሳዊ እውቀት አላቸው። በዚህም ይበልጡናል፤ የተጻፈ ቃል ኪዳን የላቸውም፤ እርስ በርሳቸው ግን ተበላልተው አያልቁም፤ ማ ዕበል ከመከሰቱ በፊት ይሸሻሉ፤ እሳተ ገሞራ ከመፍለቅለቁ በፊት ራሳቸው ከስፍራው ያርቃሉ። ይኹንና በማወቅና በምክንያታዊነት  እንበልጣቸዋለን ብለን ጉራችንን የምንቸረችረው እኛ – እኛ የሰው ልጆች ግን ወንድሞቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ ልጆቻችንን፣ ወገኖቻችን፣ ዜጎቻችንን – ሕግ አውጥተን “የሕግ የበላይነትን ለማስከበር” በሚል ሰበብ እናሰቃያለን፣ እንገርፋለን፣ በጥላቻ እርስ በርስ እንጠላለፋለን፣ እንጠፋፋለን፣ እንገዳደላለን። መቼ ነው እውቀታችን ከዚህ ድንቁርና ነጻ የሚያወጣን?

ቸር ሰንብቱ!

ምንጭ፡- ማማ

“የኢትዮጵያ ሕዝብ የቱ ነው?”

ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ

(ሸክም የበዛበት ትውልድ፡2009 እና

የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ)

Leave a Reply