
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ከፍተኛ ተወካዮች ለሦስት ቀናት የሚቆይ የምክክር ስብሰባ ናይሮቢ ውስጥ እንደሚያደርጉ ተነገረ። ከዛሬ ረቡዕ ታኅሣሥ 12/2015 ዓ.ም. ጀምሮ አስከ አርብ ድረስ እንደሚካሄድ የተነገረው ንግግር ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም፣ ደቡበ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ውስጥ የተፈረመውን ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ትግበራን የሚመለከት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
Source: Link to the Post