የኢትዮጵያ መንግሥት “የውጭ ሀገር ሰዎች የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ” የሚፈቅድ ሕግ እያዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች ቤት እንዲገዙ የሚፈቅደው…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/XGZZKtdRqJsN7WQ-K365TFgxdGzLpSFHoy0I2NvYabDOclrjZMJbVB0xw9Wm8Kt_NlIkoDaNQxwIIrL2I21iASdSB84-DWrkOO8DTWxT1dmcVR00xzhGYvbZH1kfrS0PI368VqBo1y9iAck1dGtEyS6ydxozKneO8Ih5C73v17gMWjmftfNJBZ9J-Tdj-XHVoQ8J3iKjwKdV9D59kRjCOQI5RgnwmpvcTgeQrFdduDBEZgZaxGvHq80BjUbX1eZXinyCO5TcVRO2JsGJI3t9Rf9fRr1zyW_9I2Wn_RNrjXgYvK5HouM6oBfbiJnGSdv0uTAj3uLJUAlT5STc4QPWjg.jpg

የኢትዮጵያ መንግሥት “የውጭ ሀገር ሰዎች የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ” የሚፈቅድ ሕግ እያዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች ቤት እንዲገዙ የሚፈቅደው ሕግ ዝግጅት “የመጨረሻው ደረጃ ላይ” እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከሌላቸው በቀር የንብረት ባለቤት እንዳይሆኑ የሚከለክለው አሰራር እንደሚቀየር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተናገሩት “ታማኝ” ከተባሉ ግብር ከፋዮች መካከል ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

መንግሥት  በሚቆጣጠሯቸው መገናኛ ብዙኃን ትላንት ቅዳሜ ምሽት በተላለፈው ማብራሪያ ዐቢይ በመቋቋም ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ “ቢበዛ በሁለት ወራት ውስጥ” ሥራ እንደሚጀምር ተናግረዋል።

ካፒታል ገበያው ሥራ የሚጀምረው የኢትዮ-ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ በማቅረብ ይሆናል።

መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply