የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይፈታ የሚያደርገው ምርጫ ተዓማኒ እንደማይሆን ፋይናንሻል ታይምስ ከትቦታል ( አሻራ ፣ የካቲት05/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር) የእንግሊዙ ፋይናንሻ…

የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይፈታ የሚያደርገው ምርጫ ተዓማኒ እንደማይሆን ፋይናንሻል ታይምስ ከትቦታል ( አሻራ ፣ የካቲት05/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር) የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይፈታ የሚያደርገው ምርጫ ተዓማኒ እንደማይሆን አስፍሯል፡፡ በጽሑፉ በአገሪቱ ባለፉት ቅርብ ወራት የፌዴራል መንግሥት ከትህነግ ጋር የገቡበትን ሁኔታ ያነሳው ጋዜጣው፣ መንግሥት በአገሪቱ ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ መንሥኤው ትህነግ መሆኑን ቢገልጽም በአገር አቀፍ ደረጃ ንግግር ካልተጀመረ አሁንም ቢሆን በሌላ አካባቢ ሊከሰት እንደሚችል ጠቁሟል። ፋይናንሻል ታይምስ ጨምሮም አሁን በሥራ ላይ ባለው የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎችም መፍትሔ መፈለግ እንደሚበጅ መሆኑን አመላክቷል። ሙሉ መረጃውን አሻራ ዩቱዩብ ቻናላችን ላይ ያገኛሉ፡፡ ዘጋበ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply