You are currently viewing የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ወደ' ትግራይ ክልል' እንዲገባ የህወሓት ታጣቂዎች የያዟቸውን የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ሲል አሳሰበ።          ባህርዳር:- መጋቢት 20/…

የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ወደ' ትግራይ ክልል' እንዲገባ የህወሓት ታጣቂዎች የያዟቸውን የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ሲል አሳሰበ። ባህርዳር:- መጋቢት 20/…

የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ወደ’ ትግራይ ክልል’ እንዲገባ የህወሓት ታጣቂዎች የያዟቸውን የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ሲል አሳሰበ። ባህርዳር:- መጋቢት 20/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል መንግስት ግጭት የማቆም ውሳኔ ማሳለፉ ከትግራይ ክልል በኩልም በጎ ምላሽ መሰጠቱ ይታወሳል። ነገር ግን ውሳኔ ከተላላለፈበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ምንም አይነት ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ እንዳልቻለ የክልሉ ባለስልጣናት አሳውቀዋል። ክልሉን ወክለው ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት ፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ወደግጭት ማቆም እንዲደረስ ብዙ ጥረት አድርጓል፤ የባለፈው ሳምንት ስምምነት ዝም ብሎ የመጣ ስምምነት አይደለም ብዙ ጊዜ የተሰራበት ስምምነት ነው ብለዋል። የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ክልሉ ለምን እንዳልገባ የተጠየቁት ፕ/ር ክንደያ ፤ ኃይላቸው በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች የእርዳታ መኪናዎች ስላልደረሱ ማወቅ እንዳልቻሉ ፤ ለምን እንዳልተላኩ መላክና ማሳለፍ የሚገባቸው አካላት ማብራሪ ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። ከባለፈው ሃምሌ ወር በየዕለቱ 100 የሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንደነበረባቸው የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ይገልፃሉ አሁን ያለው ችግር ሲታይ ፍላጎቱ ጨምሯል ሲሉ አስረድተዋል። አሁን ያለው ግጭት ለማቆም እና ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ የሚለው ውሳኔ ካልተሳካ ለረጅም ጊዜ ተዘጋግቶ መጠበቅ ስለማይቻል ሌላ አማራጭ እናያለን ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ እርዳታ ወደክልሉ እንዲገባ የህወሓት ኃይሎች ከያዟቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቀው ሊወጡ ይገባል ብሏል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፤ ” … እነሱ ግጭት እናቆማለን ብለው አልነበር እንዴ ? ቀደም ብሎ መንግስት የትኛውም አይነት ትንኮሳ እንደማይፈፅም እና የትኛውም አይነት ግጭት ውስጥ እንደማይገባ አስቀምጧል። በአንፃሩ እነሱ እርዳታው በቀላሉ ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ በጉልበት ከያዟቸው የአፋር ክልል ወረዳዎች መውጣት አለባቸው ብሎ አስቀምጧል። እስከዛሬ ድረስ ከ5 ወይም 6 ወረዳዎች አልወጡም። እንደውም ትላንትና ‘ኮኖባ’ በሚባል ቦታ ከአፋር ሚሊሻ ጋር ጦርነት ነበር። ለህዝቡ ካሰቡ ከያዙት ቦታ መውጣት እና መንገዱን ክፍት ማድረግ አለባቸው። ይሄን ሳያደርጉ መንግስት ሆን ብሎ ነው የሚለው ትክክል አይደለም ” – መጋሌ ፣ -ኤሬብቲ ፣ – በርሃሌ፣ -አብዓላ የተባሉ የአፋር ቦታዎችን የ ” ህወሓት ኃይሎች ” ተቆጣጥረው እንደሚገኙ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ” … ይሄ በዋናነት እርዳታው የሚሄድበት የአስፓልት መንገድ ላይ ነው ያለው። ይሄንን መልቀቅ አለባቸው ይሄንን ሳይለቁ ‘ መንግስት እርዳታ አላቀረበም ‘ ብለው ቅሬታ ማቅረብ ሚችሉበት ምንም አይነት ሁኔታ የለም። ስለዚህ እርዳታው ወደ ህብረተሰቡ እንዲደርስ ለህብረተሰቡ የሚያስቡ ከሆነ በጉልበት ከያዟቸው አካባቢዎች መልቀቅ ነው ያለባቸው፤ አካባቢውን ከግጭት ነፃ ነው ማድረግ ያለባቸው ። ” ሲሉ ዶ/ር ለገሰ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ፤ እርዳታ ለማድረስ ያለውን ዝግጅቱነት በመተመለከተ 3 የነዳጅ እና 20 የእርዳታ እህል የጫኑ 23 መኪናዎች ቆመዋል (ከዚህ በፊት ሄደው በፀጥታ ችግር የተመለሱ) ፤ በተጨማሪ ሰመራ ላይ ከመጋዘን ለመጫን የሚጠባበቁ ትልልቅ ተሽከርካሪዎችም አሉ በአጠቃላይ 43 ተሽከርካሪዎች ናቸው መንገዱ ካልተከፈተ እና ግጭት ካልቆመ እርዳታ ሊሄድ አይችልም ብለዋል። መንግስት የወሰነው ለሰብዓዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ እስከመቼ እንደሚቆየ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ፤ ” በመንግስት በኩል የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የለም። ህብረተሰቡ ወደ ተለመደው ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመጣ ነው መንግስት የሚፈልገው ፤ አካባቢውም ተረጋግቶ መጪውም ክረምት ስለሆነ እርሻውን እንዲያርስ መንግስት የሚፈልገው ከዛ ውጭ የሚደረግ ነገር ካለ እሱን በሂደት ይታያል። ” ብለዋል ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply