“የኢትዮጵያ መንግስት ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሰላም ነው። በማንኛውም ጊዜ ድርድር ይደረጋል።”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ሐሙስ ሰኔ 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ መንግስት ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሰላም ነው። በማንኛውም ጊዜ ድርድር ይደረጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።

ከምክር ቤቱ አባላት ከህወሃት ቡድን ጋር ይደረጋል ስተለተባለው ድርድር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ለሰላም ነው። በማንኛውም ጊዜ ድርድር ይደረጋል ብለዋል።

ምክንያቱም ሲያስረዱ፤ “ጥላቶቻችን እነዚህ በውስጥ ያሉ ሀይሎችን በመጠቀም አገራችንን እየጎዱ ነው። ስለዚህ ይህንን ከምንጩ ለማድረቅ የንግግር እድል ካለ እርሱን እንጠቀም ነው ዋናው ምክንያቱ። ድርድሩ ይሳካል አይሳካም ሂደቱ ይወስነዋል። ለንግግር ክፍት መሆን ግን ችግሩ አይታይኝም።” ሲሉም ገልፀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply