የኢትዮጵያ መንግስት ደሴና ኮምቦልቻን ነፃ ማውጣቱን አስታወቀ

https://gdb.voanews.com/2C62DA76-DA21-4460-9EF9-38B2D2066DC1_w800_h450.jpg

የአማጺው የትግራይ ኋይሎች ተቆጣጥረዋቸው የነበሩትና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ተንታኞች “ቁልፍ” ስፍራ ናቸው የተባሉት ደሴና ኮምቦልቻን የኢትዮጵያ መንግሥት ነፃ ማውጣቱን ማምሻውን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል የሚገኙት ደሴ እና ኮምቦልቻን እንዲሁም ባቲን ጨምሮ በምስራቅ ግንባር የሚገኙ በርካታ ከተሞች በኢትዮጵያ በመንግስት የጸጥታ ኋይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply