የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/W1SKK263Ks-7019tz5jlvUdNAkTmFI3S2uGFNxs1l2ZNa-PBlS_3AC_xpxdApsjvZi_Z4OWIz--4wLZSB0Gzn9MzmjSIsLAiVLI2wB4iugy_2GV9Zt8JFNQF7g0daV2wLBeLlvoaaYwAM7QGrAWvP9mIIBfeAvdtmv0Ht1EWi1UasU38HKVovVzlOJVJadhxFQ3pKJDUQjKwwwDwezqjmlcdudE1V7HNV7C-kMYA1WlsjIvsomve0yEK2qRNNj6rqvU4UIHQwHzIcOimjFk5P9N_QkruWrwiGwgrGsjXlp2hi4MC8n2hT-fkSKZFxSFRKUD-8qv8_RvSy3lvcdWHfw.jpg

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

ይህንን ሲያደርግም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውጊያ ሳይደረግ የህወሓትን ወታደራዊ ዐቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ተጠቅሟል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብአዊ የርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ እየሠራ ይገኛል።

የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እንዲያፋጥኑ እያደረገ ነው።

ከየአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሕዝባዊ አስተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እያመቻቸ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኅብረት በኩል በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር የሚሳተፍ ይሆናል።

አጋጣሚውንም የሰላም ንግግሩን ግጭቱን በሰላም ለመፍታት የሚቻልበት ዕድል አድርጎ ይመለከተዋል።

በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት እየተስተካከለ የመጣውን ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር አድርጎ ይወስደዋል።
በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል።

ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

@ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply