የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ያልሰበሰበዉ ዕዳ እንዳለዉ ገለጸ፡፡ጥቁር አንበሳን ጨምሮ ሌሎች ትልልቅ የመንግስት ሆስፒታሎች ዕዳቸዉን በጊዜ መክፈል አልቻሉም…

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ያልሰበሰበዉ ዕዳ እንዳለዉ ገለጸ፡፡

ጥቁር አንበሳን ጨምሮ ሌሎች ትልልቅ የመንግስት ሆስፒታሎች ዕዳቸዉን በጊዜ መክፈል አልቻሉም ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት በብድር በሰጠዉ መድሃኒት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ያልሰበሰበዉ ዕዳ መኖሩን አስታዉቋል፡፡

በጊዜዉ ዕዳን ካለመክፈል ጋር ተያይዞ 91 የህክምና ተቋማት የህግ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉ ተገልጿል፡፡

ከእነዚህ መሃል 80 የህክምና ተቋማት ክፍያቸዉን የፈጸሙ ሲሆን፤ 11 ተቋማት ደግሞ በህግ መጠየቃቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በህግ ጥያቄ ከቀረበባቸዉ 11 ተቋማት መካከል 2ቱ ትልልቅ ተቋማት በስተመጨረሻ ዕዳቸዉን መክፈል መቻላቸዉ ተነስቷል፡፡

ቀሪ 9ኝ ተቋማት ደግሞ በክስ ሂደት ላይ በመሆናቸዉ ጉዳዩ ሲያልቅ የሚከፍሉ መሆናቸዉን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተናግረዋል፡፡

ከ32 ትልልቅ ሆስፒታሎች ጋር ዉል የተገባለት አሰራር መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ አገልግሎቱ መድሃኒት ያቀርባል ተቋማቱ ደግሞ ገንዘቡን በተባለዉ ጊዜ ገቢ ያደርጋሉ፡፡

እነዚህ 32 ሆስፒታሎች የመድሃኒት ክፍፍል ላይ 76 በመቶ ድርሻ አላቸዉም ነዉ የተባለዉ፡፡

ተቋሙ አሰራሩ ይህ ቢሆንም ግን የአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ትልቅ ችግር መኖሩን ያነሱት ደግሞ የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አወል ሃሰን ናቸዉ፡፡

አቶ አወል ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንደነገሩን በዱቤ ላይ ዱቤ የማንፈቅድ ቢሆንም ፤ መድሃኒት ወስደዉ ገንዘቡን የማይከፍሉ ተቋማት በመበራከታቸዉ ተቸግረናል ነዉ ያሉት፡፡

ባለፈዉ 2015 ዓ.ም በተገላባጭ ፈንድ 8 ቢሊየን ብር መድሃኒት መሸጡን አስታዉሰዉ ከዛ መሃል 6 ሚሊየኑ በብድር የተሸጠ መሆኑን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply