የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ መቀሌ ቅርንጫፍ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ መቀሌ ቅርንጫፍ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ገብረማርያም አስታውቀዋል፡፡ቅርንጫፉ መሠረታዊ የሕይወት አድን መድኃኒቶችን፣ የኤች.አይ.ቪ፣ የቲቪ፣ የክትባት መድኃኒቶችንና ሌሎችንም ማሠራጨቱን ተናግረዋል፡፡ስራ አስኪያጁ በመቀሌ ከተማና በአካባቢው ለሚገኙ የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ መድኃኒት ማሠራጨቱንና ለውቅሮ፣ ለአዲግራትና ለሞህኒ አካባቢዎች በአሁኑ ሠዓት መድኃኒቶች መሠራጨት መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

ቅርንጫፉ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸውን መድኃኒቶች ከህዳር 28 ጀምሮ ያሰራጨ ሲሆን ከ53 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የጤና ፕሮግራም፣ ከ10 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የመደበኛ ግዥ፤ በአጠቃላይ ከ63 ነጥብ 8 ሚሊዬን ብር በላይ መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያዎችን ከዋናው መ/ቤት ወደ መቀሌ ቅርንጫፉ በመጓጓዝ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

**********************************************************************************

ዘጋቢ፡ ሰላም በቀለ

ቀን 17/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply