የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ምክር ቤት ስራ መጀመሩን አስታወቀ።ምክር ቤቱ ለአንድ አመት ያህል የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ሲያጠና…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/puqXHFYlT3RnjjOIAbghdEcWU6n3xUPhv0_h7i71zvZuaD2EjqBrmT91UNgdbveS5rOCyVP0VOcd9cBTn9oJToF3dFi62v6tZmy5EtjpdI9UAp5kB6PZXzXWMpfGoGW4NWav-aXtszne53_hzsLFSjV9pfP_PEx9ZnuLB46juS8r0T9b7vXu8dYe1uWcO-jaPDTMbSkWUS8AJwiGBWyGHrKxA6IdI8NKCz8TuBu3P1SbcYM3IA3oGD4cGZk4jyGeVcKAoiWfJG6vp8EtTHNY13zMtRO1Q8P7-UyodF40g0t_4n9LCR20MEwCbncF7G-M0BQi6kKBvwkDbc4QLZ773Q.jpg

የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ምክር ቤት ስራ መጀመሩን አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ለአንድ አመት ያህል የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንና በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ሲያጠና እንደነበር ተናግሯል።

ለማስታወቂያ ድርጅቶች የሚከፈለው ኮሚሽን አነስተኛና የተለያየ መሆን፣ የስራቸውን ውጤትም በሰዓቱ አለመክፈል እንዲሁም ከህግና መመሪያ ውጭ በራሳቸው መስራትና ሌሎችም ችግሮች እንዳሉ ተረድቻለሁ ብሏል ፤ ምክር ቤቱ።

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት እና የማስታወቂያ ባለሙያ አቶ ሳምሶን ማሞ፣ ይህ ምክር ቤት የማስታወቂያው ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ለዘርፉ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የማስታወቂያ ኢንዲስትሪው የመንግስት ድጋፍ እንዳላገኘ የገለጹት አቶ ሳምሶን ለፕሮዳክሽን የሚያገለግሉ መሳሪያዎች እንደ ቅንጦት እቃ እየታዩ የሚጠየቅባቸው የቀረጥ ክፍያ ከፍተኛ መሆኑ አግባብ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።

ምክር ቤቱ የማስታወቂያ ስራን ጥራት ለመመዘን የሚያስችል አሰራር መዘርጋት እና ሙያተኞችን ማብቃት ላይ ትኩረት በማድረግ የማስታወቂያ ኢንዱስትሪውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ይሰራልም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ምክር ቤት በእያንዳንዱ የማስታወቂያ ድርጅት ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ለመፍታት አቅም የሚፈጥር መሆኑን ያነሱት አቶ ሳምሶን፣ የማስታወቂያ ድርጅቶች ኑ በጋራ ሆነን መብታችንን እናስከብር ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 02 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply