የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የኦንላይን ግብይት ሊጀምር መሆኑን ገለጸ፡፡የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከዚህ በፊት ያገበያይ የነበረበትን የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት በኦንላይን ለመቀየር እየሰራ መሆኑን ሰምተ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Bmnuh0KBXwswa4YVom_36jYLagYESBHdjGouVDDBTmmqehAZktOJg4sBfUsWP_hegZs9iLkrv3fQUMrusI9FeHhqfMk-gtUq_1rUw74O_GbSqz-vzeVY_Yi8dsZv7p7rhm-mdj654LBsoUHQYMtnbj0t8p3sWisCCpyAMHUNsO7laaAOnb0i_QxkSP9CZgntvEZujvwwJnlSMH0yvKoQ5aC2BIyZ7wYfJCqrbrG9V7cecnbMmYEq4pPOL6wR-yttW2AO6tbSMyjeOHu_5O09isawDHNL_1QBZAtytdO53vnszg6vCSqgkEMQkSrcSOn2QauT8dpQKSoyDKAlXgIgYw.jpg

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የኦንላይን ግብይት ሊጀምር መሆኑን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከዚህ በፊት ያገበያይ የነበረበትን የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት በኦንላይን ለመቀየር እየሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የምርት ገበያዉ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ዳዊት ሙራ፤ ከሚቀጥለዉ ዓመት ጀምሮ በኦንላይን የግብይት ስርዓት ማገበያየት እንደሚጀመር ነግረዉናል፡፡

ከዚህ በፊት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ባሉ 6 የኤሌክትሮኒክስ የመገበያያ ማዕከላት ደንበኞች ወደ ተቋሙ ሳይመጡ መገበያየት ይችሉ እንደነበር ገልጸዉ፤ አሁን ላይ ግን ወደ የትኛዉም ማዕከል መምጣት ሳይጠበቅባቸዉ ባሉበት ሆነዉ መገበያየት የሚችሉበትን ስርዓት ከሚቀጥለዉ ዓመት ጀምሮ ለማስጀመር መታሰቡን ነዉ የነገሩን፡፡

እስካሁን ባለዉ ሂደት ሶፍትዌር እያበለጸጉ መሆናቸዉን ገልጸዉ፤ ግልጽ የሆነ ጊዜ ባያስቀምጡም በሚቀጥለዉ ዓመት ግን አገልግሎት መስጠት እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡

ምርት ገበያዉ በዚህ ዓመት 11 ወራት ጊዜ ዉስጥ ከ23.7 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸዉን ከ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ማገበያየቱንም አቶ ዳዊት ነግረዉናል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በቀጣይ ዓመት ኑግ፣ ባቄላ እና ሽምብራን በአዲስ መልክ ማገበያየት እንደሚጀምር የገለጹት ሃላፊዉ፤ የቢራ ገብስ ለማገበያየት የሚያስችል ረቂቅ አልቆ ወደ ስራ መገባቱንም ነግረዉናል፡፡

ከተመሰረተ 16 ዓመት የሞላዉ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እስካሁን ድረስ ከ3መቶ84 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸዉን 8 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እህል ማገበያየቱንም ለማወቅ ችለናል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply