
የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን የካቲት 12! የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በዚያ ቀን፣ ልክ የዛሬ 86 ዓመት፣ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በተካሄደው ጭፍጨፋ አዲስ አበባና አካባቢዋ ውስጥ ብቻ ወደ 30 ሺህ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀን፣ ዘንድሮ 86ኛ ዓመቱ ላይ ነው። የካቲት 1929 ዓ.ም. ያህል ለኢትዮጵያ የመከራና የጽልመት ወራት ኖሮ አያውቁም። በጣም የሚገርመው፣ በዚሁ በወርኃ የካቲት 1888 ዓመተ ምህረትም ከሰባ ሺህ በላይ ወገኖቻችንን መሥዋዕት አድርገናል። ግፈኛው የንጉሥ ኡምቤርቶ ጦር፣ በጄኔራል ባራቴሪ እየተመራ ሃይማኖት ሊቀለብስ፣ መሬት ሊቆርስ፣ ነፃነታችንን ሊገስ መጥቶ ማጭድና ጎራዴ፣ ጦርና ጋሻ የያዙትን በመድፍና በዘመኑ መሳሪያዎች ፈጃቸው።  ከአርባ አንድ ዓመታት በኋላ ተመልሶ ለወረራ የመጣው በማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ የሚመራው የፋሺስትም ጦር፣ ከየካቲት 12 ቀን እስከ የካቲት 14 ድረስ ባሉት ሦስት ቀናት ከሠላሳ ሺህ በላይ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን ገደላቸው።  ዕለቱን ሀገር ውስጥ ያሉ ብቻ ሳይሆኑ ከአገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በተለያየ ዝግጅቶችና ፕሮግራሞች በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታትን በማሰብ ልናከብራቸው ይገባናል። የመታሰቢያ ሐውልታቸው የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በይፋ ማክበር የተጀመረው በ1934 ዓ.ም ነው። በዚያን ጊዜ የነረውም ሃውልት፣ ይህ ዛሬ ትከሻውን አሳብጦ፣ ደረቱን ገልብጦ ቆሞ የምናው ሃውልት አልነበረም የተተከለው።  የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በይፋ ማክበር የተጀመረው በ1934 ዓ.ም ነው። በዚያን ጊዜ የነረውም ሃውልት፣ ይህ ዛሬ ትከሻውን አሳብጦ፣ ደረቱን ገልብጦ ቆሞ የምናው ሃውልት አልነበረም የተተከለው። ያኛው ሃውልት እስከ 21ኛው የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ማለትም፣ እስከ 1950 ዓ.ም ድረስ ለመታሰቢያነት ሲያገለግል ቆየ በኋላ፣ በ22ተኛው የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ይኼኛው የመታሰቢያ ሃውልት በዩጎዝላቪያ መንግሥት ርዳታ በ1951 ዓ.ም በይፋ ተመረቀ። በዚህም መሠረት የሥነ-ሃውልትና የቅርጻ-ቅርጽ ባለሙያዎች ከዩጎዝላቪያ መጥተው ይህ ዛሬ የምናየው ሃውልት በመጀመሪያው ሃውልት ስፍራ ላይ ተተካ። 6 ኪሎ የሚገኘውን የሰማዕታት ሀውልት ቆሞ ስናየው ምን ይሰማን ይሆን ? #ክብር_ለሰማዕታት #ቢኒያምታደለ #ተከፍሎልናል #fypシ #ኢትዮጵያ #የካቲት_12 #ሰማዕታት “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post