የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የመንግስት ሰራተኞችን የግብር ቅነሳን በተመለከተ ላቀረበው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘሁም አለ፡፡

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ግብር ቅነሳን በተመለከተ ለፍትሕ ቢሮ በደብዳቤ ላቀረብው ጥያቄ እስካሁን ፈጣን ምላሽ እንዳላገኘ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን አስታውቋል።

የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተለያዩ ተቋማት አቅጣጫ ቢሰጡም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ እንደሌለ ተናግረዋል።

አቶ ካሳሁን አቅጣጫ ለተሰጠው የፍትህ ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጠን በደብዳቤ ብናሳውቅም ከተቋሙ እስካሁን ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተለን ነው ያሉት አቶ ካሳሁን ምላሹ ከዘገየም ሌላ አማራጭ እንደሚጠቀሙም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ለሰራተኞች የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል እንዲቀመጥና ሰራተኛው ላይ የተጫነው ግብር እንዲቀነስ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መጠየቁ ይታወሳል።

በለአለም አሰፋ
የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply