የኢትዮጵያ ሰባዊ መብቶች ጉባኤ- ኢሰመጉ በመተከል አብዛኛውን የሞቱት ሴቶች እና ህፃናት ናቸው አለ፡፡ (አሻራ ጥር 5፣ 2013 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ሰባዊ መብቶች ጉባዔ ከህዳር 15 እስከ…

የኢትዮጵያ ሰባዊ መብቶች ጉባኤ- ኢሰመጉ በመተከል አብዛኛውን የሞቱት ሴቶች እና ህፃናት ናቸው አለ፡፡ (አሻራ ጥር 5፣ 2013 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ሰባዊ መብቶች ጉባዔ ከህዳር 15 እስከ ጥር 4 ድረስ ያልተቋረጠ የሰው ልጆች ጅምላ ጭፍጨፋ ተደርጓል ብሏል፡፡ አብዛኛውን የተጨፈጨፉትም ሴቶች እና ህፃናት ናቸው ብሏል፡፡… በሌላ በኩል የመተከሉ ቀብር አስፈፃሚ ኮማንድ ፓስት ማህበራዊ ሚዲያው መረጋጋት እንዳይፈጠር አድርጓል የሚል ግምገማ ዛሬ በግልገል በለስ ከተማ አድርጓል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በግልገል በለስ ስለ ማህበራዊ ሚዲያው ሲያወራ ከ40 በላይ ንፁሃን በግፍ ተገለዋል፡፡ ኮማንድ ፓስቱ ስለተገደሉት ሚዲያ እንዳያወጣው ቢፈልግም በማህበራዊ ሚዲያው ጫና ተገዶ ታጣቂው እየተደመሰሰ ነው የሚል ማላገጫ አውጥቷል፡፡ ይህን ቢልም ግን የመንግሥት ሚዲያዎች ሳይቀሩ ንፁሃን ሲሞቱ ኮማንድ ፖስቱ ድረስ እየተባለ እንዳልደረሰ እየዘገቡ ነው፡፡ ኮማንድ ፓስቱ የገዳዮች ሽፋን ሰጭ መሆኑ እና የሴራ ፖለቲካ ምርኮኛ መሆኑ በህዝብ አመኔታ አሳጥቶታል፡፡ ነገ በሚሰጠው መግለጫም ማህበራዊ ሚዲያውን አውግዞ፣ መተከል ሰላም ነው ለማለት አልሟል፡፡ የግምገማ ሀሳቡ ይሄ ነው፡፡ የኮማንድ ፓስቱ አለቃ ጠቅላይሚኒስትሩ ቢሆኑም ቁርጠኛ አመራር አለመስጠታቸው ፣ እያስወቀሳቸው ነው፡፡ ህወኃት የተሸነፈው በኢሳያስ መሪነት እንጂ በአብይ አይደለም የሚል ሀሜትም እየመጣ ነው፡፡ የኤርትራ ወታደሮች ያልገቡበት መተከል እና ወለጋ አልተረጋጋም፡፡ ስለዚህ የአብይ አህመድ አመራር ሶስተኛ አካል የሚፈልግ ከሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ሀይል ያስፈልጋል እያሉ ነው፡፡ ኢንጂነር ይልቃል የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል ካልገባ ጅምላ ጭፍጨፋው መፍትሄ ላያገኝ ይችላል የሚል አውድ ያለው ሀሳብ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴያቸው አስፍረዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply