የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች የፊልም ፌስቲቫል!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያዘጋጀው የ2ኛው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች የፊልም ፌስቲቫል በተለያዩ ከተሞች ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ፍፃሜውን ያገኛል፡፡

ዘንድሮ ከመጀመሪያው ዙር በተለየ መልኩ በተለያዩ አምስት ከተሞች በተለያዩ ቋንቋዎች የተሰሩ ፊልሞችን በመተርጓም፣ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ሲሉ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ወ/ሮ ራኬብ መሰለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በፌስቲቫሉ የተለያዩ ርዕሶች ዙረያ የተሰሩ ፊልሞች ቀርበው ወይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በሴቶችና ህፃናት፣በአካል ጉዳተኞች፣ በአረጋውያን እንዲሁም ከፍልሰት እና ስደት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ፊልሞች ቀርበው ሰዎች ለስደት ያላቸውን አመለካከት በተመለከተ ለማስተማር ይረዳል ተብሏል፡፡

ፌስቲቫሉ በአዳማ፣በሀዋሳ፣ባህርዳር እና ጅግጅጋ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ፍፃሜውን ያደርጋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 18ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply