የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሥራ ለመጀመር የሚያስችለውን 1.5 ቢሊዮ ብር ማግኘቱን አሳወቀ። የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን ኢሲማኤል እ…

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሥራ ለመጀመር የሚያስችለውን 1.5 ቢሊዮ ብር ማግኘቱን አሳወቀ።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን ኢሲማኤል እንደገለፁት በህዳር ወር 2016 ዓ.ም የተጀመረው ባለሀብቶችን የማግባባትና የማሳመን ሥራ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ባለሀብቶች ከተጠበቀው በላይ በማግኘት 1.5 ቢሊየን (26.6 ሚሊየን ዶላር) ካፒታል ማሰባሰብ ተችሏል ።

ዶ/ር ጥላሁን በገበያ የድርሻ ተሳትፎ ካደረጉ የውጭ ተቋማት መካከል ኤፍ.ኤስ.ዲ አፍሪካ፤ የትሬድና ዴቨሎፕመንት ባንክ ግሩፕ (ቲዲቢ)ና የናይጄሪያ ኤከስቼንጅ ግሩፕ (አን.ጂ.ኤክስ ግሩፕ) ያሉ ባለሀብቶች ናቸው ብለዋል ።

ከሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ደግሞ 16 የግል የንግድ ባንኮችን፤ 12 የግል የኢንሹራንስ ድርጅቶችንና 17 ሌሎች የሀገር ውስጥ ተቋማዊ ባለሀብቶችን ያካተተ መሆኑን ሰምተናል።

በመሆኑም በመጀመሪያ ከታቀደው የብር 631 ሚሊየን (11.07 ሚሊየን ዶላር) ካፒታል፤አሁን የተገኘው በ240% የሚበልጥ ነው።

በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በድምሩ 48 በፋይናንስና ከፋይናንስ ዘርፍ ውጪ ባሉ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ተሳትፎ አድርገዋል ነው የተባለው።

በተጨማሪም የሰነደ መዓለ ንዋዮች ገበያው በመጪዎቹ ወራት ወደሥራ ለማስገባት የገበያውን ሕገደንብ፣ ግብይትን ተግባራዊ ለማድረግ ይሰራል ተብሏል ።

በተጨማሪም የቴከኖሎጂ መሠረተ ልማት የቴከኒከ ግምገማ ማጠናቀቁንና የኢንቨስተሮች የትምህርት ማዕከልን ለማቋቋም እየሰራ መሆኑ ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ግብይት በኢትዮጵያ መንግስትና በግሉ ዘረፍ የተቋቋመ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ልዑል ወልዴ
መጋቢት 26 ቀን 2016

Source: Link to the Post

Leave a Reply