የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት በመጪው 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በታዛቢነት እና ለመራጮች ትምህርት ለመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አስታውቋል፡፡

በምርጫ ወቅት የሲቪክ ማህበራት የበኩላቸውን ኃላፊነት የሚወጡበት አሰራር ተዘርግቶላቸው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅትም ሴቶች ከድምፅ መስጠት እስከ ተመራጭነት ያላቸው ተሳትፎ እንዲጨምር እየሰራ ስለመሆኑ የጥምረቱ የፕሮጀክት ባለሙ ወይዘሮ ዮዲት ለማ አስረድተዋል፡፡

ሴቶች በመራጭነት በሚስተፉበት ወቅት ችግራቸውን የሚፈታ ሃሳብ የያዘውን ፓርቲ በመመዘን መሆን እንዳለበት ገለፀው ይህ እንዲሆንም ግንዛቤን ማዳበር ላይ ማተኮራቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ከዚህ በፊት የነበረውን አሰራር ማለትም ሴቶች በግፊት እንዲመርጡ ሲደረግ የቆየውን ለመቀየር እና ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጣ ፓርቲን በእውቀት በመታገዝ እንዲመርጡ ትምህርት በመስጠት ላይ ነን ብሏል ቅንጅቱ፡፡

ቀን 03/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply