የአፍሪካ አህጉር ታዋቂ አስር ባንኮች ፎቶግራፍ በደረጃቸው ይስተዋላል
የኢትዮጵያ ባንኮች በዘር ፖለቲካ መፎካከር ኃላቀርነት ነው! ከዓለም አገራቶችና አፍሪካ ባንኮች ጋር በዶላር፣ ዩሮ፣ፓውንድ ወዘተ ይወዳደሩ እንጂ ወንዝ በማያሻግር ብር መፎካከር ባዶነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ባንኮች ባህር ማዶ ሃገራት ቅርንጫፍ ባንኮች በመክፈት ከውጭ ባንኮች ጋር በመወዳደር፣ በዓለም አቀፍ ንግድ በመፎካከር፣ በውጪ ንግድ ገቢያችንን ከፍ በማድረግ፣ የውጪ ምንዛሪ ተቀማጭ ገንዘብ በማከማቸት፣ የዲጆታል ባንኪንግን ቴክኖሎጂን በመቅሰም ተወዳዳሪና ተፎካካሪ መሆን ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡ በተመሳሳይ በምድረ ኢትዮጵያ የውጪ ሃገር ባንኮች ገብተው እንዲሠሩ በመድረግ ዓለም አቀፍ ንግድ ድርጅት (World Trade Organization) አባል መሆን አይቻለናል፡፡
“እስካሁን ድረስ ሲካሄድ የነበረው ትርክት ሲያበረታታ የነበረው የዘር ፖለቲካ መሆኑ፣ በባንክ ዘርፉ ብቻ ሳይሆን፣ በአገር ደረጃ እንዲሰርፅ ሲሠራ በመቆየቱ እሱን ማላላት አለብን ይላሉ፡፡ ምንያቱም ተወዳዳሪነትና ፉክክሩ መሆን ያለበት የኢትዮጵያ ባንኮች ከሌሎች የኬንያ፣ የቱኒዝያ፣ የዑጋንዳ፣ የናይጄሪያና የሌሎች አገሮች ባንኮች እንጂ ደቡብ፣ አማራ ኦሮሞ እየተባለ አይደለም በማለት ባንኮች ሰብሰብ ብለው ተወዳዳሪ ባንክ መፍጠር እንዳለባቸው መክረዋል፡፡ ኬንያ ካሉ ባንኮች እንወዳደር ቢባል ምን ያህል እንጓዛለን፣ የእኛ በጣም ትንንሾች ናቸው፡፡ ለውጪው ውድድር መዘጋጀት አለብን፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አገራችን ውስጥ ሁልጊዜ በውጭ ኢንቨስትመንት ተደግፈን መኖር እንደማይቻል በመረዳት፣ የራሳችን ጠንካራ ኢንቨስተሮች፣ ትልልቅ ገንዘብ የሚያበድሩ ተቋማት መፍጠር አለብን ብለዋል፡፡” አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ፡፡
የኢትዮጵያ አንድ ለእናቱ ባንክ፣ ከአፍሪካ አህጉር ታዋቂ ባንኮች ጋር ጠቅላላ ንብረቱና ካፒታሉ ሲነፃፀር!
በ2020 እኤአ የአፍሪካ አሃጉር ታዋቂ አስር ባንኮች በጠቅላላ ንብረት እና የባንክ ካፒታል ደረጃቸው ተቀምጦል፡፡ በዚህም መሠረት ከአንድ እስከ አስር ባሉ ባንኮች ውስጥ ታላላቆቹ የደቡብ አፍሪካ ባንኮች አንደኛ ደረጃ ስታንደርድ ባንክ ግሩፕ ፣ ሁለተኛ ኤቢኤስኤ ግሩፕ፣ ሦስተኛ ፈርስት ራንድ ባንክ፣ የአራተኛነት ደረጃ የግብፅ ባንክ ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት፣ አምሰተኛ ደረጃ ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ (ደቡብ አፍሪካ ናቸው፡፡ የሞሮኮ ባንክ ታላላቅ ሦስት ባንኮች ውስጥ ስድስተኛ ደረጃ አቲጃርኢዋፋ፣ ሰባተኛ ደረጃ ግሩፕ ባንኪዩ ፖፑላር፣ እና አስረኛ ደረጃ ቢኤምሲኢ ባንክ ግሩፕ ናቸው፡፡ የአልጀሪያ ባንክ ሁለት ታላላቅ ባንኮች ውስጥ ስምንተኛ ደረጃ ባንኪዩ ናሽናሌ ደ አልጅሪያ፣ ዘጠነኛ ባንኪዩ ኤክስቲሪየር ድአልጀሪያ፣ አስረኛ ደረጃ ቢኤምሲኢ ግሩፕ ሞሮኮ ሲሆኑ፣ የአስራሰባተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ አንድ ለእናቱ ባንክ፣ ከአፍሪካ አህጉር ታዋቂ ባንኮች ጋር ጠቅላላ ንብረቱና ካፒታሉ ሲነፃፀር!
#1 – ስታንደርድ ባንክ ግሩፕ (ደቡብ አፍሪካ) STANDARD BANK GROUP (SOUTH AFRICA) – ጠቅላላ ንብረቱ 162 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የባንኩ ካፒታል አስራአንድ ቢሊዮን ዶላር፣ ሃምስ ሽህ ሠራተኞች ያሉት ባንክ ነው፡፡ 1120 ቅርንጫፎች፣ 6775 ኤቲኤም ና ኤኤን ኤኤስ ማሽኖች አሉት
#2 – ኤቢኤስኤ ግሩፕ (ደቡብ አፍሪካ) ABSA GROUP (SOUTH AFRICA) – ጠቅላላ ንብረቱ 83 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የባንኩ ካፒታል ስድስት ቢሊዮን ዶላር፣ አርባ ሁለት ሽህ ሠራተኞች ያሉት ባንክ ነው፡፡ ባንኩ በ12 አገራቶች ውስጥ ይሰራል፡፡
#3 –ፈርስት ራንድ ባንክ (ደቡብ አፍሪካ) FIRSTRAND BANK (SOUTH AFRICA) – ጠቅላላ ንብረቱ 92 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የባንኩ ካፒታል አምስት ነጥብ አራት ቢሊዮን ዶላር፣ አርባ ዘጠኝ ሽህ ሠራተኞች ያሉት ባንክ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ፣ በእንግሊዝ፣ በህንድ ቅርንጫፎች አሉት
#4 – ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት (ኢጂፕት) NATIONAL BANK OF EGYPT (EGYPT) –የግብፅ ብሔራዊ ባንክ ጠቅላላ ንብረቱ 97 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የባንኩ ካፒታል አምስት ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ዶላር፣ 510 ቅርንጫፍ ባንኮች አሉት፣ 14 ሚሊዮን ደንበኞች አሉት
#5 – ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ (ደቡብ አፍሪካ) NEDBANK GROUP (SOUTH AFRICA) –ጠቅላላ ንብረቱ 76 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የባንኩ ካፒታል አምስት ቢሊዮን ዶላር፣ ሠላሳ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሠራተኞች ያሉት ባንክ ነው፡፡ 692 ቅርንጫፍ ባንኮች አሉት፣ 4240 ኤቲኤም ማሽኖች አሉት
#6 – አቲጃርኢዋፋ (ሞሮኮ) ATTIJARIWAFA (MOROCCO) – የሞሮኮ ባንክ ሲሆን ጠቅላላ ንብረቱ 56 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የባንኩ ካፒታል አምስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር፣ በ25 አገራቶች ውስጥ ይሠራል፣ 10 ሚሊዮን ደንበኞች አሉት ‹‹በራሳችሁ ተማመኑ›› የሚል መፈክር አለው፡፡
#7 – ግሩፕ ባንኪዩ ፖፑላር (ሞሮኮ) GROUPE BANQUE POPULAIRE (MOROCCO) –የሞሮኮ ባንክ ሲሆን ጠቅላላ ንብረቱ 45 ቢሊዮን ዶላር፣ የባንኩ ካፒታል አራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር፣ በ40 አገራቶች ውስጥ ይሠራል፣ 20 በመቶ የፈረንሳይ የንዋይ ኢኮኖሚን ይቆጣጠራል
#8 – ባንኪዊ ናሽናሌ ደአልጀሪያ Banque Nationale d’Algerie (Algerie) የአልጀሪያ ባንክ ሲሆን ጠቅላላ ንብረቱ 26 ቢሊዮን ዶላር፣ የባንኩ ካፒታል ሦስት ቢሊዮን ዶላር፣
#9 – ባንኪዊ ኤክስተሪኢር ደአልጀሪያ Banque Exterieure d’Algerie (Algerie) የአልጀሪያ ባንክ ሲሆን ጠቅላላ ንብረቱ ? ቢሊዮን ዶላር፣ የባንኩ ካፒታል ሦስት ቢሊዮን ዶላር፣
#10 – ቢኤምሲኢ ግሩፕ ሞሮኮ BMCE Bank Group Morocco የሞሮኮ ባንክ ሲሆን ጠቅላላ ንብረቱ 33 ቢሊዮን ዶላር፣ የባንኩ ካፒታል 2.7 (ሁለት ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር፣
#17 – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ኢንባ) (የኢትዮጵያ) Commercial Bank of Ethiopia የመንግሥት ባንክ ሲሆን፣ ጠቅላላ ንብረቱ 25 ቢሊዮን ዶላር፣ የባንኩ ካፒታል 1.7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር፣ 67 (ስልሳ ሰባት ሽህ) ሠራተኞች ያሉት ባንክ ነው፡፡ኢንባ አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 3,083 (ሦስት ሽህ ሰማንያ ሦስት) አሉት፡፡ በአፍሪካ የባንኪንግ ፋይናንሻል ዘርፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአስራ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
“Following a large recapitalisation in 2018, government-owned Commercial Bank of Ethiopia moves up one place to #17 in the overall ranking and dominates the regional ranking (see below) with Tier 1 capital of $1.7bn, total assets of $25bn and net profits of $397m.” …………(1)
በ2021 እኤአ (2013ዓ/ም) የባንኩ አጠቃላይ ሀብት በ19 በመቶ አድጎ 934 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግረዋል፡፡ በሪፎርሙ የተገኘው ውጤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውጤት ብቻ ያለመሆኑን፣ የብዙ ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ዕገዛ ታክሎበት እንደሆነም አስምረውበታል፡፡ አሁን በዘጠኝ ወር ያስመዘገበው ውጤት ጥሩ ነው ቢባልም፣ ብዙ የሚቀረው ስለመሆኑ የሚገልጹት አቶ ተክለወልድ፣ ባንኩን ለመለወጥና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ማኢንዚ የተባለ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አማካሪ ተቋም በጨረታ አወዳድሮ በመቅጠር ወደ ሥራ መግባቱ ባንኩን የበለጠ እንደሚለውጠው ተናግረዋል፡፡ (1 United States Dollar equals 42.30 Ethiopian Birr) (934,000,000,000/ 42.30=22,080,378,250.591) የባንኩ አጠቃላይ ሀብት በ19 በመቶ አድጎ 934 ቢሊዮን ብር ወይም ሃያ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ተገልፆል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአፍሪካ የፋይናንሻል ባንኪንግ ዘርፍ ጋር በጠቅላላ ንብረቱና ካፒታሉ ሲነፃፅር ለመረዳት በቀላሉ የቀረበ ባንኮችን የማወዳደሪያ ጥናት መሠረት፡-
- ስታንደርድ ባንክ ግጉፕ፤– የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ንብረቱ 25 (ሃያ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ስታንደርድ ባንክ 162 (መቶ ስልሳ ሁለት)ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ ስታንዳርድ ባንክ ኢንባ ከስድስት እጥፍ በላይ ይበልጣል፡፡የኢንባ ካፒታል7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ስታንዳርድ 11 (አስራአንድ) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ስታንዳርድ ባንክ ኢንባ ከስድስት እጥፍ በላይ ይበልጣል፡፡አውቶማቲክ ቴለር ማሽኖች (ኤቲኤም) 3,083 (ሦስት ሽህ ሰማንያ ሦስት) ሲኖሩት ስታንዳርድ ባንክ 6775 ኤቲኤም ና ኤኤን ኤኤስ ማሽኖች አሉት ስታንዳርድ ባንክ ኢንባ ከሁለት እጥፍ በላይ ይበልጣል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ሁሉም ባንኮች ተደምረው ስታንደርድ ባንክ አያክሉም፡፡
- ኤቢኤስኤ ግሩፕ:-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ንብረቱ 25 (ሃያ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ኤቢኤስኤ ባንክ 83(ሰማንያ ሦስት)ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ኤቢኤስኤ ባንክ ኢንባ ከሦስት እጥፍ በላይ ይበልጣል፡፡የኢንባ ካፒታል7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ኤቢኤስኤ 6 (ስድስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ኤቢኤስኤ ባንክ ኢንባ ከሦስት ተኩል እጥፍ በላይ ይበልጣል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ሁሉም ባንኮች ተደምረው ኤቢኤስኤ ባንክ አያክሉም፡፡
- ፈርስት ራንድ ባንክ፡––የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ንብረቱ 25 (ሃያ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ፈርስት ራንድ ባንክ 92(ዘጠና ሁለት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ፈርስት ራንድ ባንክ ኢንባ ከሦስት ነጥብ ሰባት በላይ ይበልጣል፡፡የኢንባ ካፒታል7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ፈርስት ራንድ 5.4 (አምስት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ፈርስት ራንድ ባንክ ኢንባ ከሦስት እጥፍ በላይ ይበልጣል፡፡ የኢትዮጵያ ሁሉም ባንኮች ተደምረው ፈርስት ራንድ ባንክ አያክሉም፡፡
- ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት:-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ንብረቱ 25 (ሃያ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የግብፅ ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት ባንክ 97 (ዘጠና ሰባት)ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት ባንክ ኢንባ ከአራት እጥፍ ይበልጣል፡፡የኢንባ ካፒታል7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት 5.3 (አምስት ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት ባንክ ኢንባ ከሦስት እጥፍ በላይ ይበልጣል፡፡ የኢትዮጵያ ሁሉም ባንኮች ተደምረው ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት አያክሉም፡፡
- ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ:-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ንብረቱ 25 (ሃያ አምስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ ባንክ 76 (ሰባ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ ባንክ ኢንባ ከሦስት እጥፍ በላይ ይበልጣል፡፡የኢንባ ካፒታል7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ 5 (አምስት) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ ባንክ ኢንባ ከሦስት እጥፍ ይበልጣል፡፡ የኢትዮጵያ ሁሉም ባንኮች ተደምረው ኤንኢዲ ባንክ አያክሉም፡፡
የኢትዩጵያ መንግሥት የባንክ ዘርፉን፣ ከዓለም አቀፍና ከአፍሪካ አህጉር የባንኮች ውድድር ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ያለ አንዳች ፉክክር ስለጠበቃቸው ብዙ ትርፍ እያገኙ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ከውጭ ባንኮች ጋር በፍፁም ሊወዳደሩ አይችሉም፡፡ የአፍሪካ ባንኮች ከውጭ ባንኮች ጋር አብሮ በመሥራት ዘመናዊ የባንክ ቴክኖሎጂን በመቅሰም ክህሎታቸውን በማዳበርና በባህር ማዶ አገራትም ቅርንጫፍ ባንኮች በመክፈት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱበት ዘመን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ባንኮች ደግሞ ከዓለም አቀፍና ከአፍሪካ አህጉር የባንኮች ውድድር በመነጠላቸው የተነሳ ቴክኖሎጅን በመሳብ፣ አዳዲስ አሰራሮችን በመፍጠር ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን አቅም አጥተዋል፡፡ በአንፃሩ የእኛ ባንኮች ደካማ ስለሆኑ ከአፍሪካ አህጉር የባንኮች ጋር የመወዳደር አቅም አይኖራቸውም፡፡ የአፍሪካ ባንኮች በኢትዮጵያ ያሉ የሁሉም ባንኮች ጠቅላላ ንብረትና ማቌቌሚያ ካፒታል ተደምሮ ከሦስት እስከ ስድስት እጥፍ እንደሚበልጡ በወሬ ሳይሆን በመረጃው ሰነድ አይተናል፡፡ ለዚህ ነው በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች ቢገቡ የሃገር ውስጥ ባንኮች ከጨዋታ ውጪ እንደሚሆኑ እራሳቸው የሚመሰክሩት፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ አዲስ ባንክ ለማቌቌም የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል
‹‹የዛሬ ሃያ ስምንት አመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንክ ለማቌቌም የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል አሥር ሚሊዮን ብር ነው የሚል መመርያ አወጣ፡፡ የመጀመርያዎቹ የግል ባንኮችም በዚሁ ሁኔታ ተመሥርተው ወደ ሥራ ሊገቡ ችለዋል፡፡›› ‹‹ ከዚህ በኃላ የባንክ ማቌቌሚያ የካፒታል መጠን ወደ 20 (ሃያ) ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ተደርጎል፡፡ በሒደት ወደ 100 (መቶ) ሚሊዮን ብር አደገ፡፡ የዛሬ አስር አመት ደግሞ የባንኮቹ የማቌቌሚያ ካፒታል 500 (አምስት መቶ) ሚሊዮን ብር ሆኖል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ከሚገኙ 16 የግል ባንኮች ውስጥ አብዛኞቹ የተቌቌሙት በመቶ ሚሊዮን ብርና ከዚህ በታች ካፒታል ያስፈልጋል በሚለው መመርያ ነው፡፡››
‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠኑን ከ500 ሚሊዮን ብር ወደ 5 ቢሊዮን ብር ማሳደጉም ከገንዘብ ግሽበትና አቅም ጋር እንዲሁም ከኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጋር የተገናዘበ ካፒታል ባንኮች ሊኖራቸው ይገባል ከሚል ነው፡፡ የባንክ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠኑ 5 ቢሊዮን ብር እንዲሆንና ይህንንም ካፒታል ነባር ባንኮች በአምስት ዓመት፣ በምሥረታ ላይ ያሉ ባንኮች ደግሞ በሰባት ዓመት ያሟሉ ከሚለው ሰሞናዊ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ጋር ተያይዞ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ተዋንያንን በተለያየ ምልከታም እያነጋገረ ነው፡፡ በአብዛኛው መመርያው አግባብና የሚጠበቅም ነው የሚል አስተያየት የተሰጠበት ቢሆንም፣ ……………….…(2)
በ2021 እኤአ የአፍሪካ አህጉር ውስጥ የሚገኙ አስር ምርጥ ባንኮች በአፍሪካ አህጉርና በዓለም አቀፍ ከተሞች ቅርንጫፍ ያሎቸው ባንኮች ናቸው፡፡ የአፍሪካ አህጉር ውስጥ 1.3 (አንድ ቢሊዮን ሦስት መቶ ሚሊዮን) ህዝብ ይኖራል:: ከዓለም ህዝብ 17 (አስራ ሰባት) በመቶውን ይሸፍናል፡፡ በአህጉሪቱ ውስጥ 54 ሃምሳ አራት አገሮች ይገኛሉ፡፡ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ታይምስ ባጠናቀረው መረጃ መሠረት የአስሩ ጠቅላላ ንብረት 600 (ስድስት መቶ) መቶ ቢሊዮን ዶላር ሲገመት አራት አገሮች ስም ብቻ በሊስቱ ውስጥ ሲገኝ የደቡብ አፍሪካ አምስት ባንኮች በስም ዝርዝሩ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
The Top Ten Largest Banks in the African Continent/by Richie SantosdiazJanuary 7, 2021
Home to over 1.3 billion people, the African continent is home to almost 17% of the world’s total population. According to the United Nations, Africa is home to 54 countries. Each of them is unique and diverse, presenting their own cultural and economic differences. In terms of banking, the region as a whole has various unique players that cater to its large population.
The Fintech Times compiled the top ten largest banks in the African continent and ranked them (based on asset. Combined, our top ten list would be valued at over $600 billion USD. Interesting fact, only four countries in Africa as a whole are represented in the Top Ten list; in fact, one country alone holds five places on the list.According to their various corporate websites in terms of company description, here are a brief synopsis of each of the top ten banks:
ከመንግሥት ፖለቲካ መር ወደ የግል ዘርፍ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ሚናና መሪነት መሸጋገር
‹‹አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ፣ ታዋቂው የፋይናን ባለሙያ ሀገሪቱ የምትመራበት የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዬች ፍኖተ ካርታ አለመኖር ‹‹ ከለውጡ ወዲህ አገሪቱ የምትመራበት የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ምን እንደሆነ አለመታወቁ ችግር ነው፣ ኢኮኖሚውን የሚመራው ፍኖተ ካርታ ከሌለ ከችግሮች ተላቆ መራመድ እንደሚቸግር ያሳስባሉ፡፡… እስከዛሬ የነበረው አካሄድ መንግሥት መር የሆነ አቅጣጫና ኢኮኖሚውን የሚመራው ፖለቲካው ነበር፡፡ አሁን ግን ኢኮኖሚው ሊመራ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ በእስከዛሬው ጎዞ ትልቅ ድክመት ኢኮኖሚውን የሚያወዛውዘው ፖለቲካው መሆኑን፣ … አሁን ግን ይህ መቅረት አለበት ብለዋል፡፡ … ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የግሉ ዘርፍ ሚናና መሪነት የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ በተግባር ያስፈልጋል፡፡››
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሻገተ የፖለቲካ ካድሬ አመራር
‹‹ባንኩ ሥር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል ከተባለ የሰው ኃይሉንም መፈተሽ አስፈላጊ በመሆኑ፣ የሰው ኃይል ፖሊሲውም እየታየ ነው፡፡ ቦርዱ ከዚህ ቀደም አንድ ሺሕ ተተኪ አፍርተናል የሚል ሪፖርት ተመልክቶ የነበረ ሲሆን፣ ወደ ውስጥ ሲገባ ግን የተተኪ ድርቀት ያለበት መሥሪያ ቤት መሆኑ ታይቷል፡፡ 67 ሺሕ ሠራተኛ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከዚህ ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ባለዲግሪ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ማስተርስ ያላቸውን ቢሆኑም የተተኪ ድርቀት አለበት፡፡…….የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደስሙ ኢትዮጵያን መምሰል እንደሚገባው አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ባንኩ የአንድ ክልል ምክር ቤት ወይም ካቢኔ ሊሆን ስለማይችል ከሁሉም የተውጣጣ ሠራተኛ መኖር መሆን አለበት ብለዋል፡፡››………………….…(3)
የጡብና አዳፍኔ ዘመን ባንከኛው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የዲጂታል ባንኪንግ ዘመን ባንከሮችን ሞራል ለመስበር ያደረጉት የፖለቲካ ካድሬ ንግግር የሻገተ አስተሳሰብ ነው እንላለን፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሲያስጨንቁ የነበሩት ሰባት መቶ ሰባ አራት ቢሊዮን ብር የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የብድር ዕዳ፣ ተጠያቂው ማን ነው? አላዋቂ ዕዳ ሰራዥ በህዝብ ያልተመረጠ መንግሥት፣ አንድ ቀን ከእናንተ ጋር ለፍርድ ይቀርባል? ወርቅ ቅብ ባሌስትራ የሚረከብ አመራር መቼ ነው ለፍርድ የሚቀርበው?፣ ወለጋ ሃያ ሦስት ባንክ ሲዘረፍስ? የኢትዮጵያ የባንክ አመራሮች በሪፖርታቸው እንኳን አላነሱትም፡፡ አንድ ቀን ለባንክ አመራሮች የፍርድ ቀን ይመጣል እንላለን ፡፡ በኤቲኤም ማሽኖች ስርጭት ከዓለም 179 አገራቶች ኢትዮጵያ 178ኛ ደረጃ አገኘች! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሻገቱ አመራሮች ወርቅ ቅብ ላሜራ የኢህአዴግና ግራዋ ብልፅግና የፖለቲካ ካድሬ ቡችሎች የተገኘ ውጤት ወደፊት በዲጂታል ባንኪንግ የተማሩ ወጣቶች ይሻሻላል፡፡
‹‹በሪፎርም ሥራ ውስጥ ሲገባ የልማት ድርጅቶች የቀድሞ ብድር፣ አዲስ ሥራዎች ላይ ብድር መስጠት የሚሉት ጉዳዮች ችግር የገጠማቸው ነበሩ፡፡ አቶ ተክለወልድ እንዳሉት፣ ይህንን የከፋ ችግር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ከገንዘብ ሚኒቴርና ከማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ጋር ውይይት በማድረግ እንዲቀረፍ ባይደረግ ኖሮ የባንኩ ዕጣ ፈንታ አሳዛኝ ይሆን ነበር፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሲያስጨንቁ የነበሩት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የብድር ዕዳ፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የመሳሰሉ ችግሮች በመንግሥት ውሳኔ መፍትሔ ባያገኙ ባንኩ ሊወጣቸው የማይችሉ ነበሩ፡፡… ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመኖርና ያለመኖር አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቶ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለልማት ድርጅቶች የሚሰጠው ብድር ነበር፡፡ ይህ ለልማት ድርጅቶች የተሰጠው ብድር ከባንኩ አጠቃላይ ብድር 85 በመቶ የያዘ ሲሆን፣ ብድሩ በማንኛውም ሁኔታ ሊከፈል ያልቻለ፣ በቀጣይም ቢሆን ብድሩ የመመለሱ ሁኔታ አደጋች የነበረ ነው፡፡››…………….(4)
‹በመመሥረት ላይ ያሉ ባንኮች አደራጆችም የተለየ የባንክ ሞዴል (ቢዝነስ ሞዴል) በመቅረፅ የአክሲዮን ገዥዎችን ቀልብ ከመሳብ ይልቅ፣ ምንም ክህሎት የማይጠይቀውን ያለፈው መንግሥት የዘራውን ክፉ ዘር አካባቢያዊነትን ብቻ በመጠቀም የአንድ ብሔርን፣ ጎሳንና ቋንቋን ስያሜን በማድረግ በቀላሉና በአቋራጭ አክሲዮኖችን ይቸበችባሉ፡፡ ግባቸው በእንትን ብሔር የሚጠራ ባንክ መመሥረት ብቻ ይመስላል፡፡ በዚህም በፖለቲካው ሜዳ ያለው የብሔር ብሔረሰቦች ትከሻ መለካከት በባንክ ኢንደስትሪውም ዘልቆ ‹‹እኛም አለን ባንክ›› ማን ከማን ያንሳልን እያየን ነው፡፡ ምስኪኑም ኅብረተሰብ በዚህ ሙዚቃ ተስቦ በስሜት ብሔሩ ስለተጠራ ግራ ቀኝ ሳይል አቤት አለሁ እያለ መቀነቱን ፈቶ፣ በሽሚያና በግፊያ አክሲዮኖችን ይገዛል፡፡ ምን የተለየ ነገር ይዘዋል? አሁን ያሉት ባንኮች እንዴት ናቸው? ውድድሩ? አትራፊነትታቸው? ኢንዱስትሪው ከፊቱ ያለው መልካም ዕድልና ተግዳሮት የሚሉና የመሳሰሉትን ወሳኝ ጥያቄዎችን አብዛኞቹ አደራጆችና አክሲዮን ገዥዎችም አይጠይቁም፡፡ መለኪያው፣ መመዘኛው፣ ወሳኙም ነገር በብሔሩ፣ በጎሳው፣ በአካባቢው ስም ብቻ ይጠራለት አለቀ ደቀቀ፡፡ እንግዲህ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ተቆጣጣሪ አካል ኢንዱስትሪው በዕውቀት፣ በቴክኖሎጂና በአጠቃላይ በንግድ ውድድር ብቻ እንዲመራ የፖለቲካው ፉክክር እዚያው በሜዳው እንዲሆን ማድረግ ይገባዋል፡፡ ዋነኛ ኃላፊነቱም ነው፡፡›› ………………..(5)
ምንጭ፡-
(1) Africa’s Top 100 Banks 2020: East Africa – African Business
(2)ጥያቄ ያስነሳው አዲሱ የባንክ ማቋቋሚያ ካፒታል/ 28 April 2021
https://www.ethiopianreporter.com/article/21938አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ
(3) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖና የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ/ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማዳን ጉዞ/2ሜይ 2021
(4) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመሩን አስታውቋል/5 May 2021
(5) ጸሐፊው የባንክ ባለሙያ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡