የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር የኮሮና ቫይረስ የደህንነት መስፈርት ባለማሟላቱ ለአገልግሎት ክፍት እንዳይሆን ታገደ።የቴአትር ቤቱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ከፈለኝ ለኢትዮ ኤፍ…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር የኮሮና ቫይረስ የደህንነት መስፈርት ባለማሟላቱ ለአገልግሎት ክፍት እንዳይሆን ታገደ።

የቴአትር ቤቱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ ከፈለኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ህዳር መጀመሪያ ላይ የቴአትር ቤቱን 65ኛ አመት አስመልክቶ ለአገልግሎት ክፍት ልናደርግ ነበር ብለዋል፡፡

ነገር ግን ከጤና ጥበቃ ሚንስቴር መጥተው በጎበኙበት ወቅት ትያተር ቤቱ የጤና ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ፕሮቶኮሎችን ባለማሟላቱ በቅርቡ እንዳይከፈት ማዘዛቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ቴአትር ቤቱን ምቹ ለማድረግ በመጪው ረቡዕ ጽዳት እንደሚጀመር ሰምተናል፡፡

ቴአትር ቤቱ ስራ ሲጀምር 3 ቴአትሮች የተመረጡ ሲሆን 10 ያልበለጡ ተዋናዮች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡

በኮሮና ምክንያት ቴአትር ቤቱ በመዘጋቱ የቋሚ ተቀጣሪዎች ደሞዝ አልተቋረጠም ያሉት አቶ በፍቃዱ የተጋባዥ ተዋንያን ደሞዝ መቋረጡ እንዳሳሰባቸውም ተናግረዋል፡፡

ትያትር ቤቱ መች እንደሚከፈት በውል ያልታወቀው ሲሆን መስፈርቱን አሟልቶ ሲከፈት አዳራሹ ከሚችለው አንድ አራተኛው እንደተፈቀደለት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply