የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለት ፓርቲዎችን ፈቃድ ሰረዘ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለት ፓርቲዎችን ፈቃድ ሰረዘ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሰረት ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተጠየቁት መካከል አራት ፓርቲዎች መስፈርቱን ያሟሉ ሲሆን ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ባለሟሟላታቸው መሰረዛቸውን ገልጿል፡፡

የተጠየቀውን መስፈርት ያሟሉ ፓርቲዎች ፤የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/- የአፋር ሕዝብ ፓርቲ /አሕፓ/፤ የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ጋዴፓ/ እና የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ /አነግፓ/ ናቸዉ፡፡ የሚጠበቅባቸዉን መስፈርቶች ባለሟሟላታቸው ደግሞ ፤ የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /መኦሕዴፓ/ የመስራች ፊርማ ናሙና ማረጋገጫ ከ35 በመቶ በታች በመሆኑ እና የ1 ሺህ 142 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ ተሰርዟል፡፡

ሁለተኛዉ የተሰረዘዉ ፓርቲ የሲዳማ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሲብዴፓ/ ሲሆን – 778 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ያልተሟላ በመሆኑ እና በምስክርም ስለመረጋገጡ የቀረበ ነገር ባለመኖሩ ነው የተሰረዘው ብሏል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply