የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለበርካታ ዓመታት ሲጠቀምባቸው የነበሩትን መዛግብቶች ለብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃሕፍት ኤጀንሲ አስረከበ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃሕፍት ኤጀንሲ በተለያዩ ጊዚያት የሚገኙ መዛግብቶችን በማሰባሰብ እና በመረከብ ለትውልድ የማቆየት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ከብሔረሰቦች ጥናት ኢንስቲትዩት ሲጠቀምባቸው የነበሩትን በርካታ ቁጥር ያላቸው መዛግብቶችን ለኤጀንሲው አስረክቧል፡፡

በርክክብ መርሃ-ግብሩ ላይም የብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃሕፍት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ይኩኡነአምላክ መዝገቡ እነዚህ መዛግብቶች ተጠብቀው ቆይተው ወደ ኤጀሲው በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

እነዚህ ተጠብቀው የቆዩ መዛግብቶች የሀገርን ገፅታ የሚገነቡ በመሆናቸው ወደ ትክክለኛ ቦታቸው በመመለሣቸው መደሰታቸውን የገለፁት ደግሞ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሣቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሣ ናቸው፡፡

*********************************************************************************

ቀን 13/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply