የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸዉን ግዴታዎች ያላሟሉ ፓረቴዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን አስታዉቋል፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸዉን ግዴታዎች ያላሟሉ ፓረቴዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን አስታዉቋል፡፡ በዚህም 26 ፓረቲዎች በቦርዱ ሚጠበቅባቸዉን ባለማሟላታቸዉ መሰረዛቸዉ ታዉቋል፡፡ ሁሉም ፓለቲካ ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች በጽሁፍ እንዲደርሳቸው እንዲሁም ማምጣት ያለባቸውን ተጨማሪ የመስራች ፊርማ ቁጥር በመጥቀስ እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፡፡

በዚህም መሰረት ማሟላት ያለባቸውን ሰነዶች ያላቀረቡ 26 ፓርቲዎች ተሰርዘዋል ብሏል :: የመስራች አባላትን ያቀረቡ ፓርቲዎች መካከል ሳምፕል በመውሰድ በሁሉም ክልሎች እና ሁሉም ወረዳዎች የመስራች አባላትን ማጣራት ስራ ማከናወኑን የገለጸዉ ምርጨ ቦርዱ፤ ስራው የተከናወነው በቦርዱ የክልል ቅርጫፍ ጽህፈት ቤቶች አማካኝነት ነዉ ብሏል፡፡

የማጣራት ሂደቱ ረጅም ግዜ መዉሰዱን ቦርዱ የገለጸ ሲሆን፤በተጨማሪ በሂደቱ የተገኘው የማጣራት ውጤት ቦርዱ በፈለገው መንገድ ሊሆን አልቻልም፡፡ እንደአዲስ አበባ ባሉ የአስተዳደር አካላት የመስራች ፊርማን ለማጣራት ባልቻሉበት ሁኔታ ፓርቲዎች እንዳቀረቡት ትክክለኛ ፊርማ እንዲቆጥር ተደርጓል፡፡ከዚህም በመነሳት 35 በመቶ በላይ መስራች ፊርማቸው ትክክል የሆኑ ፓርቲዎችን ምዝገባ ለማጽደቅ የወሰነ ሲሆን ፤ከ35 በመቶ በታች የሆኑ ትክክለኛ ፊርማ ያመጡ እና የተለያዩ በቦርዱ የተጠየቁትን መስፈርት ያላሟሉ ፓርቲዎችን እንዲሰረዙ ወስኗል፡። በዚህም መሰረት የመስራች ፊርማ ናሙና ማረጋገጫ ከ35 በመቶ በታች በመሆኑ የተሰረዙ ፓርቲዎች መሆናቸዉን ቦርዱ አስታዉቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply