የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስድስት ደረጃዎችን አሻሻለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስድስት ደረጃዎችን አሻሻለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊፋ በሚያወጣው ወርሃዊ የእግር ኳስ ደረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን /ዋልያዎች ስድስት ደረጃዎችን አሻሻለ፡፡

ቡድኑ ስድስት ደረጃዎችን አሻሽሎ 140ኛ ላይ መቀመጡ ፊፋ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

ብሔራዊ ቡድን ካሜሮን በምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወሳል፡፡

ቤይልጄይም፣ ፈረንሳይ ብራዚል ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ከአፍሪካ ሴኔጋል ሁለት ደረጃዎችን አሽቆልቁላ 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ቱኒዚያ 26ኛ ደረጃ በመያዝ ሁለተኛ በመሆን ስትከተል ናይጄሪያ አራት ደረጃዎችን በማሻሻል 32ኛ ላይ ትገኛለች፡፡

ጊኒቢሳው 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ቀዳሚ ስትሆን 108ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ናሚቢያ 10 ደረጃዎችን በማሻሻል 111ኛ ስትሆን አርመንያ 9 ደረጃዎችን በማሻሻል 90ኛ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በፊፋ ወርሃዊ ሪፖርት ሞዛምቢክ 11 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል ቀዳሚ ስትሆን ወደ 117ኛ ደረጃ ተንሸራታለች፡፡

ኢስቶንያ እና ሊቢያ 8 ደረጃዎችን ወርደው 116ኛ እና 119ኛ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ብሪቲሽ ቨርጅን አይላንድስ፣ ኧንጉይላ፣ ሳንማሪኖ ከ208ኛ እስከ 210ኛ ያለውን የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች መያዛቸውን ከፊፋ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስድስት ደረጃዎችን አሻሻለ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply