የኢትዮጵያ ትንንሽ የዘር ባንኮች እየተዋሃዱ፣ የተከፈለ ካፒታላቸውን አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ያሳድጉ!!! (ክፍል አራት) ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

በኢትዮጵያ 16 የግል ባንኮች የባንክ ማቋቋሚያ የተከፈለ ካፒታል፣ ለአንድ ለእናቱ አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ የተበረከተ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንክ ለማቌቌም የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል አምስት ቢሊዮን ብር ከፍ አድርጎልአምስት ቢሊዮን ብር በዶላር ሲሰላ (1 United States Dollar equals 42.30 Ethiopian Birr) በዶላር ማለት 118,203,309 (መቶ አስራ ስምንት ሽህ ሁለት መቶ ሦስት) ዩኤስ ዶላር ማለት ነው!!!  የተከፈለ ካፒታሉ አሥር ቢሊዮን ብር ከፍ ሲል 236.4 ዩኤስ ዶላር ማለት ነው!!! የተከፈለ ካፒታሉ አስራአምስት ቢሊዮን ብር ከፍ ሲል 355 ዩኤስ ዶላር ማለት ነው!!! የተከፈለ ካፒታሉ ሃያ ቢሊዩን ብር ከፍ ሲል ደግሞ 473 ሚሊዮን ዶላር ይሆላል፡፡ በዚህ ጊዜ የባንኮች ውህደት እውን ይሆናል የዘር ሃረግ ይወድቅና የዲጂታል ባንኪንግ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ እውን ይሆናልና   የኢኮኖሚ እድገትም ይመጣል እንላለን፡፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣የባንክ የተከፈለ ካፒታል ሃያ ቢሊዩን ብር 473 ሚሊዮን ዶላር ከፍ እንዲል መመሪያ በማውጣት በዘር እንአሸን የተፈለፈሉ ባንኮች ውህደት እንዲፈጥሩ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

#1 –አዋሽ ባንክ፣ (8.38) ቢሊዮን ብር .ወይም (198,109) ሚሊዮን ዶላር፣

#2 –ዳሽን ባንክ፣ (5.8) ቢሊዮን ብር ወይም(137,116) ሚሊዮን ዶላር፣

#3 – ንብ ባንክ፣ (5.23) ቢሊዮን ብር ወይም (123,641) ሚሊዮን ዶላር፣

#4 – ዩናይትድ ባንክ (4.54) ቢሊዮን ብር ወይም (107,329) ሚሊዮን ዶላር፣

#5 –ባንክ ኦፍ አቢሲኒያ፣ (4.19) ቢሊዮን ብር ወይም (99,054) ሚሊዮን ዶላር፣

#6 – ወጋገን ባንክ፣(4.17) ቢሊዮን ብር ወይም (98,582) ሚሊዮን ዶላር፣

#7– ኮኦፕሬቲቨ ባንክ ኦፍ ኦሮሚያ (3.9) ቢሊዮን ብር ወይም (92,199) ሚሊዮን ዶላር፣

#8– ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ (3.65) ቢሊዮን ብር ወይም (86,288) ሚሊዮን ዶላር፣

#9– ብርሃን ባንክ (3.03) ቢሊዮን ብር ወይም (71,631) ሚሊዮን ዶላር፣

#10– አባይ ባንክ (2.8) ቢሊዮን ብር ወይም (66,194) ሚሊዮን ዶላር፣

#11– ላየን ኢንተርናሽናል ባንክ(2.79) ቢሊዮን ብር ወይም (65,957) ሚሊዮን ዶላር፣

#12– ቡና ባንክ (2.67) ቢሊዮን ብር ወይም (63,121) ሚሊዮን ዶላር፣

#13– ዘመን ባንክ(2.46) ቢሊዮን ብር ወይም (58,156) ሚሊዮን ዶላር፣

#14– እናት ባንክ (1.61) ቢሊዮን ብር ወይም (38,062) ሚሊዮን ዶላር፣

#15– ደቡብ ግሎባል ባንክ (1.2) ቢሊዮን ብር ወይም (28,369) ሚሊዮን ዶላር፣

#16– አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ(1.13) ቢሊዮን ብር ወይም (26,714) ሚሊዮን ዶላር ፣

በኢትዮጵያ 16 የግል ባንኮች የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል 1.3  (1.360522 billion dollor) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ስታንደርድ ባንክ 11 (አስራ አንድ) ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡

  • የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ኮኦፕሬቲቨ ባንክ ኦፍ ኦሮሚያ፣ አዋሽ ባንክ፣ ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ አባይ ባንክ፣ አቢሲንያ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ ላየን ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ወዘተ ተነቅሎ፣ በኢትዮጵያዊ የባንኮች ህብር ይተካ!!!
  • የኦሮሞ የባህል ማዕከል፣ የአማራ የባህል ማዕከል፣ የሲዳማ የባህል ማዕከል፣የወላይታ፣ የትግራይ የባህል ማዕከል ወዘተ ተነቅሎ፣ በኢትዮጵያዊ ሁሉን አቀፍ የባህል ማዕከል ይተካ!!!
  • የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህገ-መንግሥት፣ የጋምቤላ፣ ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሞ ህገ-መንግሥት ወዘተ ተነቅሎ የኢትዮጵያዊ  ህገመንግሥት ይተካ!!!

የኢትዮጵያ ታዋቂ አስራ ስድስት  የግል ባንኮች ለማቌቌም የሚያስፈልገው የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል 57,538 ቢሊዮን ብር ወይም 1,360,236,407 (አንድ ቢሊዮን ሦስት መቶ ስልሳ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሠላሳ ስድስት ሽህ አራት መቶ ሰባት) ዶላር ሲሆን የቅርንጫፎች ድርሻ 71 በመቶ በሴፕቴንበር 2020እኤአ ምንጭ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  Private banks paid up capital and branch share as of September 30, 2020 (source, NBE)……………..(1)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንክ ለማቌቌም የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል አምስት ቢሊዮን ብር ከፍ አድርጎል፡፡ አምስት ቢሊዮን ብር በዶላር ሲሰላ (1 United States Dollar equals 42.30 Ethiopian Birr) በዶላር ማለት 118,203,309 (መቶ አስራ ስምንት ሽህ ሁለት መቶ ሦስት) ዩኤስ ዶላር ማለት ነው!!!  አስራ ስድስቱ ባንኮች ሁሉም የባንክ ማቌቌምያ የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል ቢያሞሉ ጠቅላላ የተከፈለ ካፒታል 1,891,252,944 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት ሽህ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት) ዩኤስ ዶላር ማለት ነው!!!

በኢትዮጵያ 16 የግል ባንኮች የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል 1.3 ቢሊዮን ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ስታንደርድ ባንክ 11ቢሊዮን ዶላር ፣ የደቡብ አፍሪካው ኤቢኤስኤ  ስድስት ቢሊዮን ዶላር፣  የደቡብ አፍሪካው ፈርስት ራንድ ባንክ 5.4 (አምስት ነጥብ አራት)  ቢሊዮን ዶላር፣  የግብፅ ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት ባንክ  5.3 (አምስት ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር፣ የደቡብ አፍሪካው ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ ባንክ አምስት ቢሊዮን ዶላር ካፒታል በብዙ እጥፍ እንደሚበልጡ ይሰተዋላል፡፡  ስለዚህ የኢትዮጵያ 16 የግል ባንኮች የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል የገንዘብ መጠን ከፍ ማለት አለበት እንላለን፡፡

የአፍሪካ አገሮች የግል ባንኮች የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል

  • ‹‹ከደቡብ አፍሪካ Southern Africa’s top banks 2020 ሃያ ታዋቂ ባንኮች ውስጥ ሰባቱ የደቡብ አፍሪካ የግል ባንኮች ሲሆኑ የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል   31,582  (ሠላሳ አንድ ቢሊዮን  አምስት መቶ ሰማንያ ሁለት) ዶላር ሲሆን አምስቱ የሞሪሽየስ  የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል   2,516 ()ዶላር፣አራቱ ሃገረ አንጎላ የግል ባንኮች  የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል   2,607 ()ዶላር ሲሆን ሁለት ሁለት ድርሻ ያላቸው  ሞዛንቢክ   819 እንዲሁም ናኒቢያ ባንክ 599 ሚሊዮን ዶላር የተከፈለ ካፒታል አላቸው፡፡
  • ሰሜን አፍሪካ North Africa’s top banks 2020 ሃያ ታዋቂ ባንኮች ውስጥ ሰባቱ የግብፅ ባንኮች ሲሆኑ የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል 15,102 ዶላር ሲኖራቸው፣ በተመሳሳይ ሰባቱ የሞሮኮ ባንኮች ሲሆኑ የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል 15,055 ዶላርተረ፣ አምስት የአልጀሪያ ባንኮች 9,365 ካፒታል እንዲሁም አንድ የቱኒዚያ 713  ሚሊዮን ዶላር ካፒታል አስመዝግበዋል፡፡
  • ምዕራብና መሃከለኛው አፍሪካ West and Central Africa’s top banks 2020 ሃያ ታዋቂ ባንኮች ውስጥ አስረሰ ሦስቱ የናይጀሪያ ባንኮች ሲሆኑ የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል 12,279    ዶላር ሲሆን፣ ቶጎ 1,692፣ ሴኒጋል 937፣ ጋቦን 860፣ አይቨሪኮስት 220 እንዲሁም ጋና ሦስት ባንኮች 679 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል እንዳላቸው አስመዝግበዋል፡፡
  • ‹‹ከምስራቅ አፍሪካ East Africa’s top banks 2020 ሃያ ታዋቂ ባንኮች ውስጥ አስሩ የኬንያ የግል ባንኮች ሲሆኑ የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል   5,820    ዶላር ሲሆን፣አራቱ የኢትዮጵያ  ንግድ ባንክ 1,738 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 326፣ አዋሽ ባንክ 249፣ ዳሽን ባንክ 202 የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል  2,515  (ሁለት ቢሊዮን አምስት መቶ አስራአምስት ሚሊዮን ) ዶላር ሲሆን፣ ሁለት የሃገረ ኡጋንዳ የግል ባንኮች 199  ሚሊዮን እና 168 ሚሊዮን የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል  367 ሚሊዮን  ዶላር ሲሆን ርዋንዳ 195 ሚሊዮን እንዲሁም ሱዳን 174 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል አላቸው፡፡ ››………….(2)

 

የባንክ ማቋቋሚያ ካፒታል 5 ቢሊዮን ብር ይሁን ሲባል ባንኮች ወደ ውህደት ሊሄዱ ችላሉ የሚል ግምት ማሳደሩ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ትንንሽ ድንክዬ ባንኮች ህብር ሆነው ካፒታላቸውን ካላሰደጉ የኢኮኖሚ እድገት አይመጣም!

ከኢትዮጵያ  Ethiopia top banks 2020 አስራ ስድስት ታዋቂ ባንኮች ውስጥ ከፍተኛውና ዝቅተኛው የባንኮች  የተከፈለ ካፒታል ከፍተኛው አራት ባንኮች ከ198 እስከ 107 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ሲኖራቸው፣ ዘጠኝ ባንኮች ከ99 ሚሊዮን እስከ 58 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል አላቸው፣ ሦስት ባንኮች 39 ሚሊዮን ዶላር በታች ካፒታል አላቸው፡፡ ዝቅተኛው 27 ሚሊዮን ዶላር የተከፈለ ካፒታል አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣የባንክ የተከፈለ ካፒታል ሃያ ቢሊዩን ብር 473 ሚሊዮን ዶላር ከፍ እንዲል መመሪያ በማውጣት በዘር እንአሸን የተፈለፈሉ ባንኮች ውህደት እንዲፈጥሩ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ከደቡብ አፍሪካ፣ የሰሜን አፍሪካን፣ ምዕራብና መሃከለኛው አፍሪካና የምስራቅ አፍሪካን አገራቶች የባንኮች የተከፈለ ካፒታልን ከድህረ ገፆች በማስተዋል የእኛን ትንንሽና ድንክዬ ባንኮች ካፒታል በጊዜው ካልተስተካከለ በሃገራችን የኢኮኖሚ እድገት እንደሚጨናገፍ  እናሳስባለን፡፡

ከደቡብ አፍሪካ Southern Africa’s top banks 2020 ሃያ ታዋቂ ባንኮች ውስጥ ከፍተኛውና ዝቅተኛው የባንኮች  የተከፈለ ካፒታል ከፍተኛው አንድ ባንክ የተከፈለ ካፒታል 11 (አስራአንድ) የተከፈለ ካፒታል የሦስት ባንኮች ደግሞ 5 (አምስት) ቢሊዮን ዶላር በላይ፣ የሦስት ባንኮች ከአንድ እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር፣ የአራት ባንኮች ካፒታል ከ500 እስከ 958 ሚሊዮን ዶላር፣ የዘጠን ባንኮች ካፒታል ደግሞ ከ500 ሚሊዮን ዶላር እስከ ዝቅተኛው 286 ሚሊዮን ዶላር ወይም (286 x42.30=8.4billion birr) ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል አላቸው፡፡ Africa’s Top 100 Banks 2020: Southern Africa – African Business

ሰሜን አፍሪካ North Africa’s top banks 2020 ሃያ ታዋቂ ባንኮች ውስጥ ከፍተኛውና ዝቅተኛው የባንኮች  የተከፈለ ካፒታል ሁለት ባንኮች ከአምስት ቢሊዮን ዶላር፣ አንድ ባንክ አራት ቢሊዮን ዶላር፣ አራት ባንኮች ሶስት ቢሊዮን ዶላር፣ አራት ባንኮች ሁለት ቢሊዮን ዶላር፣አንድ ባንክ አንድ ቢሊዮን ዶላር፣ ስምንት ባንኮች ከ886 ሚሊዮን ዶላር እስከ ዝቅተኛው 529 ሚሊዮን ዶላር ወይም  (529×42.30= 22.4birr0)፣ ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል አላቸው፡፡ Africa’s Top 100 Banks 2020: North Africa – African Business

ምዕራብና መሃከለኛው አፍሪካ West and Central Africa’s top banks 2020 ሃያ ታዋቂ ባንኮች ውስጥ ከፍተኛውና ዝቅተኛው የባንኮች  የተከፈለ ካፒታል አንድ ባንክ ሁለት ቢሊየን ዶላር፣ አምስት ባንኮች  ከአንድ ነጥብ ዘጠኝ እስከ አንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ካፒታል፣ ሰባት ባንኮች ከ937 እስከ 567ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያላቸው፣ ሰባት ባንኮች ከ500 ሚሊዮን ዶላር በታች እስከ ዝቅተኛው 164 ሚሊዮን ዶላር ወይም  (164 x42.30= 7 billion birr) ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል አላቸው፡፡ Africa’s Top 100 Banks 2020: West and Central Africa – African Business

‹‹ከምስራቅ አፍሪካ East Africa’s top banks 2020 ሃያ ታዋቂ ባንኮች ውስጥ ከፍተኛውና ዝቅተኛው የባንኮች  ከፍተኛውና ዝቅተኛው የባንኮች የተከፈለ ካፒታል የተከፈለ ካፒታል ሦስት ባንኮች ከ1.7 እስከ 1.1 ቢሊዮን ዶላር፣ሦስት ባንኮች ከ664 እስከ 569 ሚሊዮነን ዶላር ካፒታል ያላቸው፣ አስራ አራት ባንኮች ከ500 ሚሊዮን ዶላር በታች ካፒታል ያላቸው ሲሆኑ ዘቅተኛው 168 ሚሊዮን ዶላር ወይም   (168×42.30= 7.1 billion birr)  ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል አላቸው፡፡ Africa’s Top 100 Banks 2020: East Africa – African Business

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንክ ለማቌቌም የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል አምስት ቢሊዮን ብር ከፍ አድርጎል፡፡ አምስት ቢሊዮን ብር በዶላር ሲሰላ (1 United States Dollar equals 42.30 Ethiopian Birr) በዶላር ማለት 118,203,309 (መቶ አስራ ስምንት ሽህ ሁለት መቶ ሦስት) ዩኤስ ዶላር ማለት ነው!!! አስራ ስድስቱ ባንኮች ሁሉም የባንክ ማቌቌምያ የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል ቢያሞሉ ጠቅላላ የተከፈለ ካፒታል 1,891,252,944 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት ሽህ ዘጠኝ መቶ አርባ አራት) ዩኤስ ዶላር ማለት ነው!!!

በኢትዮጵያ 16 የግል ባንኮች የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል 1.3 ቢሊዮን   ሲሆን የደቡብ አፍሪካው ስታንደርድ ባንክ 11ቢሊዮን ዶላር ፣ የደቡብ አፍሪካው ኤቢኤስኤ  ስድስት ቢሊዮን ዶላር፣  የደቡብ አፍሪካው ፈርስት ራንድ ባንክ 5.4 (አምስት ነጥብ አራት)  ቢሊዮን ዶላር፣  የግብፅ ናሽናል ባንክ ኦፍ ኢጂፕት ባንክ  5.3 (አምስት ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር፣ የደቡብ አፍሪካው ኤንኢዲ ባንክ ግሩፕ ባንክ አምስት ቢሊዮን ዶላር ካፒታል በብዙ እጥፍ እንደሚበልጡ ይሰተዋላል፡፡  ስለዚህ የኢትዮጵያ 16 የግል ባንኮች የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል የገንዘብ መጠን ከፍ ማለት አለበት እንላለን፡፡

  • ሁለት ወለድ አልባ ባንኮች ዘምዘም ባንክና ሄጅራ ባንክ እንዲሁም ጎህ ቤቶች ባንክ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ አግኝተዋል፡፡ አሃዱ ባንክና የአማራ ባንክ ፍቃድ ለማግኘት በሂደት ላይ ናቸው፡፡So far two interest free banks, Zamzam and Hijra and Goh Betoch banks have secured their license from NBE to start their business, while Ahadu and Amhara are on the process to get the green light.
  • ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ለማግኘት በሂደት ላይ ያለው አዲስ የተቆቆመው የአማራ ባንክ የተከፈለ ካፒታል ስድስት ቢሊየን ብር በማድረስ ከአዋሽ ባንክ ቀጥሎ ደረጃ ይዞል፡፡The newly formed bank Amhara, which is yet to get a license from NBE, has a paid up capital of 6 billion birr placing it in second place after Awash on the paid up capital amount.

ብሔራዊ ባንክ የባንክ ማቋቋሚያ ካፒታል

  • ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (ኢብባ)፣ ለአራተኛ ጊዜ ባንክ ለማቌቌም የሚያስፈልገው የተከፈለ ካፒታል መመሪያ መሠረት የመጀመሪያው አሥር ሚሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ የመጀመርያዎቹ የግል ባንኮችም በዚሁ ሁኔታ ተመሥርተው ወደ ሥራ ሊገቡ ችለዋል፡፡›› ሁለተኛው የኢንባ መመሪያ የባንክ ማቌቌሚያ የካፒታል መጠን ወደ 20 (ሃያ) ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ተደርጎል፡፡ ሦስተኛው የኢንባ መመሪያ 100 (መቶ) ሚሊዮን ብር አደገ፡፡ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ከሚገኙ 16 የግል ባንኮች ውስጥ አብዛኞቹ የተቌቌሙት በመቶ ሚሊዮን ብርና ከዚህ በታች ካፒታል የተመሠረቱ ነበሩ:: አራተኛው የኢንባ መመሪያ የባንኮቹ የማቌቌሚያ ካፒታል 500 (አምስት መቶ) ሚሊዮን ብር ሆኖል፡፡ አምስተኛው የኢብባ መመሪያ የባንክ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠን ወደ 5 (አምስት) ቢሊዮን ብር አደረገ፡፡ The revised NBE directive, that is, the ‘minimum capital requirement for banks directive no. SBB/78/2021’that entered into force as of April 12, stated that existing banks shall raise their paid up capital to five billion birr in five years’ time until June 30, 2026. It ordered banks to come up with an action plan for capital increase within 30 days.የባንክ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠኑ 5 ቢሊዮን ብር እንዲሆንና ይህንንም ካፒታል ነባር ባንኮች በአምስት ዓመት፣ በምሥረታ ላይ ያሉ ባንኮች ደግሞ በሰባት ዓመት ያሟሉ ከሚለው ሰሞናዊ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ጋር ተያይዞ ወጣ፡፡ የአገሪቱን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ለማሳደግና የበለጠ እንዲራመድ ከተፈለ ግን የማቋቋሚያ ካፒታሉ መጠን አሁን እጅግ ዝቅተኛ ከመሆኑም

አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ ነገር ግን 5 ቢሊዮን ብር ካፒታል እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በአምስት ዓመትና በሰባት ዓመት አምስት ቢሊዮን ብር ካፒታል ይኑራቸው ማለት በእኔ ዕይታ የፋይናንስ ዘርፉ ከድሮ ጠባብ ዕይታ ያልተቀላቀለ ስለመሆኑ ያሳየኝ ነው፤›› ብለውታል፡፡………(3)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አጭር እይታና የአቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ ሩቅ እይታና 

  • ምክንያቱን ሲገልጹ ደግሞ በተለይ አሁን ካለው የብር የመግዛትና ብር ከዶላር አንፃር ካለው የምንዛሪ አቅም አንፃር ሲታይ የዛሬ አምስት ዓመት አምስት ቢሊዮን ብር የሚኖረውን የመግዛት አቅም ያላገናዘበ ውሳኔ መሆኑን የሚያሳይና የተጠቀሰው ካፒታል መጠን እጀግ አነስተኛ ነው ሲሉም ይሞግታሉ፡፡
  • ‹‹የባንኮችን ካፒታል የማሳደግ አቅጣጫ ትክክል ነው፡፡…..በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስቶክ ኤክስቼንጅ ስለሚቋቋምና የገንዘብ ማሰባሰብ ዕድልም በጣም የተሻለ ስለሚሆን ከዚያ አንፃር ካፒታልን ማሳደግ ይቻል እንደነበር አስረድተዋል፡፡››
  • ‹‹አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ ጥሩ የሚሠሩ ነባር ባንኮች አክሲዮን ለመሸጥ በምንም ሁኔታ አይቸገሩም የሚል እምነት አላቸው፡፡ ‹‹ምናልባት አንዳንዶች ከራሳቸው ባለአክሲዮኖች ውጪ አንሸጥም ካላሉ አክሲዮን ካወጡ ይሻጣሉ፡፡ ችግር የሚሆነው በስሜትና በጭፍን ሲኬድ ነው፤›› የሚል እምነት አላቸው፡፡
  • በባንኮቹ ጉዳት ላይ መንግሥት በፍፁም ተዋሃዱ ማለት የሌለበት መሆኑን በመጥቀስም፣ ባንኮቹ ራሳቸው የሚፈለግባቸውን ለማሟላት አዲስ ካፒታል ያሰባስባሉ ወይም ይዋሃዳሉ ብለዋል፡፡ ነገር ግን አሁን የተጠየቀው ካፒታል በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ አሁንም የተበታተነ የባንክ ዘርፍ ለተወሰነ ጊዜ ሊቀጥል ይችላል የሚል ግምት አላቸው፡፡ እስካሁን ድረስ ሲካሄድ የነበረው ትርክት ሲያበረታታ የነበረው የዘር ፖለቲካ መሆኑ፣ በባንክ ዘርፉ ብቻ ሳይሆን፣ በአገር ደረጃ እንዲሰርፅ ሲሠራ በመቆየቱ እሱን ማላላት አለብን ይላሉ፡
  • ምንያቱም ተወዳዳሪነትና ፉክክሩ መሆን ያለበት የኢትዮጵያ ባንኮች ከሌሎች የኬንያ፣ የቱኒዝያ፣ የዑጋንዳ፣ የናይጄሪያና የሌሎች አገሮች ባንኮች እንጂ ደቡብ፣ አማራ ኦሮሞ እየተባለ አይደለም በማለት ባንኮች ሰብሰብ ብለው ተወዳዳሪ ባንክ መፍጠር እንዳለባቸው መክረዋል፡፡ ኬንያ ካሉ ባንኮች እንወዳደር ቢባል ምን ያህል እንጓዛለን፣ የእኛ በጣም ትንንሾች ናቸው የሚሉት አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ ለውጪው ውድድር መዘጋጀት አለብን ብለዋል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም አገራችን ውስጥ ሁልጊዜ በውጭ ኢንቨስትመንት ተደግፈን መኖር እንደማይቻል በመረዳት፣ የራሳችን ጠንካራ ኢንቨስተሮች፣ ትልልቅ ገንዘብ የሚያበድሩ ተቋማት መፍጠር አለብን ብለዋል፡፡
  • ‹‹ባንኮችም ጠንካራ ካፒታል እንዲኖራቸው ይዋሃዱ ሲባል፣ አሁን እየተቋቋሙ ያሉትም ሆነ ቀደም ብሎ ከተቋቋሙት ባንኮች ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ብሔር ተኮር ስያሜ ያላቸው መሆኑ ለውህደት እንቅፋት ይሆናል የሚል አስተያየት እየተሰጠበት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር አቶ ኢየሱስ ወርቅ ትክክል ነው ይላሉ፡፡ አሁን ብሔራዊ ባንክ የወሰደው ዕርምጃ በአምስት ዓመት 15 ቢሊዮን ብር በሦስት ዓመት 10 ቢሊዮን ብር ይሁን ብሎ ቢሆን ኖሮ ባንኮች በግድ ጥምረት ይፈጥሩ እንደነበር ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም ጥምረት አድርገው አዲስ ስም በመያዝ ሊሠሩ ችላሉ፡፡ በአንድ ብሔር ስም የተቋቋመ ባንክ ከሌላ ብሔር ጋር እንዲቆራኝ ቢደረግ ይዋሃዳሉ፡፡ ግን ይህ ተግባራዊ ይሆን የነበረው ጠንከር ያለ የካፒታል መጠን ቢጠየቅ ነበር፡፡ በአምስትና በሰባት ዓመት 5 ቢሊዮን ብር አድርሱ የሚል መመርያ አውጥቶ ለማዋሃድ የሚመች አይሆንም፡፡››
  • በኢትዮጵያ አንድ የእርሻ ባንክ ያስፈልጋታል የሚሉት አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣  አንድ ኢንቨስትመንት ባንክም ሊኖራት ይገባልና እንዲህ ያሉ የባንክ ዓይነቶች ላይም ትኩረት ይሰጥ ብለዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን ባንኮች ጠንካራ ካፒታል ሲኖራቸው ነው፡፡ አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ አሁን የሚወጡ መመርያዎችም ነገን ተሻግረው መመልከት ሲችሉ ነውና ብሔራዊ ባንክ የባንክ ማቋቋሚያ ካፒታል መጠን ማሻሻል አለበት፡፡ ይህንን ለማድረግ ራሱ ነባራዊ ሁኔታው ይገፋዋል፡፡ የገንዘብ የመግዛት አቅም እየቀነሰ ሲሄድ፣ ባንክም መመርያውን ሊያሻሽል ይችላል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ባንክ ለማቋቋም አምስት ቢሊዮን ብር ያውም አምስትና ሰባት ዓመት ሰጥቶ አይሆንም፡፡ አምስት ቢሊዮን ብር ኢምንት ነው፣ መጨመር አለበት፡፡ ይህም ለባንኮችና ለአገር ጠቃሚ ነው፡፡ በተለይ እንደ አገር ጠንካራ ተወዳዳሪ ለመሆን የባንኮች ካፒታል መጠን ማደግ መሠረታዊ ነው፡፡

 

ምንጭ

https://www.ethiopianreporter.com/article/21938አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ

 

Leave a Reply