የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የቦነስ እና የደሞዝ እርከን ጭማሪ አደረገ

አርብ ነሐሴ 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተገባደደው የ2014 በጀት ዓመት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ተከትሎ ለሠራተኞች እና ከባንኩ ጋር ለሚሠሩ የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሠራተኞች ቦነስ እና የደሞዝ እርከን ጭማሪ መፍቀዱን አስታውቋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶች ምስጋና ለማቅረብ፣ እንዲሁም በአዲሱ በጀት ዓመትም መልካም ተሞክሮዎችን በማጎለበትና ለታዩ ድክመቶች የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በመቀየስ እስካሁን ከነበረው የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ሠራተኞችን ለማበረታታት ባንኩ ቦነስ እና የደሞዝ እርከን ጭማሪ መፍቀዱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበጀት ዓመቱ ከእቅድ አንጻር የ114 ነጥብ 4 በመቶ አፈፃፀም በማስመዝገብ 27 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን መግለጹ ይታወሳል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply