የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ብልሽት ምክንያት ሊሰረቅ ከነበረው ገንዘብ 78 በመቶ ያህሉን ማዳን መቻሉን ገለፀ።

ሲስተሙ በፈጠረው ችግር 801 ሚሊየን ብር ሊሰረቅ እንደተዘጋጀ ቢነሳም ወደ 600 ሚሊየን አካባቢ መመለሱን አንስተዋል።

ከአጠቃላይ ሊጠፉ ከነበረው 78 በመቶ አካባቢ ገንዘበን ማሰባሰቡ ተነስቷል

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ እንደገለፁት 26761 ደንበኞች በዛን ሌሊት ግብይት ፈፅመዋል 235293 ግብይቶች መካሁዳቸውንም አንስተዋል።

ይህም ማለት አንድ ደንበኛ ከ9 ጊዜ በላይ ግብይት መፈፀመን ተናግረዋል።

ጥፋተኞቹን ለመያዝ ብዙ አይነት መንገድ ባንኩ እንደተጠቀመ ያነሱት ፕሬዝዳንቱም ከዛ ውስጥ፣በሂሳባቸው ውስጥ በቂ ገንዘብ ያላቸውን እንዲሁም ያረጉት ግብይት ከ2 በላይ ያልሆኑ ከ10ቪ በላይ ደንበኞች ሌቦች እንዳልሆነ በማሰብ 44ሚሊየን በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ አንስተው ሁለተኛው እርምጃ ደግሞ በሂሳባቸው ውስጥ ገንዘብ አለ ነገር ግን ያላወጡ 15 ሺ ደንበኞች ወይም ከ1 ጊዜ በላይ ግብይት ያልፈፀሙ ሲኖሩ በዚህ መንገድ ሌላ ብር ሪከቨር ማድረግ እንደተቻለ ተነስቷል፡፡

አጠቃላይ በዛች ቅፅበት ከ14 ጊዜ በላይ ጊዜ ግብይት መፈፀሙ ሲነሳ ግብይቱን ከፈፀሙት ከ15000 በላይ ደንበኞች ውስጥ ሙሉ በሙሉ የከፈሉ ደንበኞች ቁጥር 9881 ሲሆን 5160 ሰዎች ደግሞ በከፊል እንዲከፍሉ እንደተደረጉ ተነስቷል፡፡

በዚህ ውስጥም 567 ደንበኞች ምንም አልመለሱም የወሰዱት ገንዘብም 9.8 ሚሊየን ብር እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ ጨምረዋል።

በግብይቱ ወቅት ያራሳቸው ካልሆነው ውስጥ ትልቁ ገንዘብ የተወሰደው ውስጥ 334 ሺ ብር እንደሆነም ተገልጿል።

ገንዘቡን ያልመለሱ ደንበኞች በዚህ ሳምንት መጨረሻ እንዲመልሱ እየተጠበቁ እንደሆነ ተነስቷል።
አሁንም እየመለሱያሉ ደንበኞች እንዳለ አንስተው ወላጆቻቸው እንዲከፍሉ እንደተደረገም እንደሆነም ተጠቁማል።

በለዓለም አሰፋ

መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply