You are currently viewing የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ሲሉ የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸ…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ሲሉ የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸ…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ሲሉ የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው በደብዳቤ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው በደብዳቤ ለንግድ ባንክ በጻፉት ደብዳቤ ቅሬታቸውን በመግለጽ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በሚከተለው ደብዳቤ ጠይቀዋል። ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አዲስአበባ ጉዳዩ፡- በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ስለመጠየቅ አገልግሎት በመስጠት ላይ የተሰማራ ማንኛውም ለትርፍ የተቋቋመ የንግድ ድርጅት በሚሰራበት አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰብን ስነ ልቦና እና እሴት ማክበር ግዴታው ነው። በዋናነት ለንግድና ለማህበረሰብ አገልግሎት የተቋቋመ በይበልጥ ደግሞ መንግሥታዊ የሆነ ተቋም የሚሰራበትን አካባቢ ማህብረሰብ የወል ፍላጎቶችን ማክበር፤ እሴትና ባህሎችን መጠበቅ ትንሹ ተቋማዊ ሀላፊነት ነው። ይህን አለማድረግ የንግድ ተቋሙ በአካባቢው ህዝብ ዘንድ በጥርጣሬ እንዲታይ ብሎም ከገበያ ውድድር መውጣትን ያስከትላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገሪቱ የፋይናንስ ተቋም ትልቁ ተቋም መሆነ ይታቃል። ስለሆነም ባንኩ በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ላለፉት ሁለት ዓመታት ከአካባቢው አስተዳደርና ህዝብ ጋር ተቀራርቦ ያለምንም የፀጥታ እንከን ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በጎንደር ዲስትሪክት በኩል ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ አንጋፋ ባንክ ለስመ ክብር የማይመጥን እና ከእውነት የራቀ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚውል ረብ የለሽ መግለጫ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በኩል አውጥቷል። ባንኩ አሰራሩን ህቡዕ በሆነ አካሄድ በመቀየር በጎንደር ዲስትሪክት ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በመካድ በሽሬ ዲስትሪክት በኩል አገልግሎቱን እንደሚሰራ አስታውቋል። በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኛ ተኮር ( customer based) የንግድ አሰራርን ሳይሆን ፖለቲካዊ አቋምና ፍላጎት የሚያራምድ ከዝንባሌም ከፍ ያለ ሚና ለማሳየት ቃጥቷል። ይህ ኢትዮጵያችን ከምትኮራበት ግዙፍ የንግድ ተቋም የማይጠበቅ፣ ለተቋሙ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ ለሚኮራው ሕዝባችን ጭምር አሳፋሪ ክስተት ነው። ተቋሙ በዚህ ሁነቱ፣ ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ለሁለት ዓመት አልግሎት ሲሰጥ የነበረ መሆኑን እያወቀ አዲስ እን ሚጀምር አስመስሎ መግለጫ ማውጣቱ ለወልቃይት ጠገዴ አማራ ያለውን ንቀት በጉልህ ገልጿል ። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ለዘመናት በዘረኛ የትግራይ ልሂቃን የዴረሰበትን ዘግናኝ ግፍ የሚያስታውሰውን አይፈልግም ብቻ ሳይሆን አምርሮ ይጠላል ይታገላል። ከባርነት ወደ ነፃነት የተሸጋገረበትን ታሪካዊ ምዕራፍ ሊያደናቅፍበት የሚፈልግን የትኛውንም ኃይል አይታገስም። ለነፃነቱ ቀናኢና ሟች የሆነው የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዘብ የባንኩን መግለጫ በፅኑ ያወግዛል። ባንኩ የታላቋ ኢትዮጵያን መጠሪያ የያዘ እንደመሆኑ መጠን ስሙን የሚመጥን ግብር (መግለጫ) ሊኖረው ይገባል ብለን እምናለን። በእስካሁኑ ቆይታውም ከዘር ኃይማኖትና ሌሎች ቡድናዊ ወገንተኝነቶች በራቀ መንገድ ኢትዮጵያዊ ቀለምና ገፅታ ተላብሶ አገልግሎት ሲሳጥ እንደነበረ እንረዳለን። ከዚህ መልካም ገፅታውና ከፍታው ሊያወርደው በሚችል መልኩ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በኩል ያወጣውን መግለጫ እንደሚያስተካክለው እምነት አለን። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ባንኩ እንደ ተቋም ፀረ-ወልቃይት ጠገዴ አማራነቱን በግላጭ እንዳሳየ ይቆጠራል። እንደ አስፈላጊነቱም መላው የአማራ ህዝበ እና ፍትህ ወዳድ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች በባንኩ ያልተገባ ሁነት ላይ ቁጣቸውን እንዲያስሙ ንቅናቄ ወደ መፍጠር ለመሻገር እንደምንገደድ እናስታውቃለን። አሸተ ደምለው ተድላ የወ/ጠ/ሰ/ሁ ዞን ዋና አስተዳዳሪ “ስንኖር በምክንያት ፣ ስንሞትም ለምክንያት”

Source: Link to the Post

Leave a Reply