የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅሬታዎችን መርምሮ ተገቢ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅሬታዎችን መርምሮ ተገቢ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቅሬታዎች መነሳታቸውን አስታውሷል፡፡

አየር መንገዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ቅሬታዎች እየተነሱ መሆኑን መገልዘቡን ገልጾ በማጣራቱ ሥራ ላይ በሚገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ በፍጥነት እንዲወሠድ ይደረጋል ብሏል።

ደንበኞቹ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች እና አስተያየቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥ በመሆኑ ሂደቱን በጥሞና ሲከታተል መቆየቱን የገለጸው አየር መንገዱ፤ የደንበኞቹን ጥቆማ ተቀብሎ አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ ይህንኑ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ ቀደም ኢትዩ ኤፍ ኤም በጉዳዩ ላይ ቅሬታ አለን የሚሉ ደንበኞችን አነጋሮ በሰራው ዘገባው ትልቁ የአገሪቱ የደህንነት ተቋም በሙስናና ብልሹ አሰራር ውስጥ በመዘፈቁ ዜጎች ብቃት ያለው አገልግሎት አጥተው በገዛ አገራቸው ለእንግልትና ለመከራ መዳረጋቸው እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰራተኞቹ ከህግ አግባብ ውጪ በሚፈጥሩት ወከባ ምክንያት ተጓዦች በረራዎች እንዲያመልጧቸው ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረው ነበር፡፡

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር የሆኑት ማስተዋል ገዳ ከተገልጋዮች የተሳው ቅሬታ እና ጥቆማ እንደደረሳቸው ገልጸው ከመስራቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ቦሌ አየር ማረፍያ ከሚገኝው የስራ ተቆጣጣሪ ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ ምክክር እየተደረገበት ነው ብለዋል፡፡

አንዳንዴ ካለመናበብ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ አለመግባባቶች መኖራቸውን የተናገሩት ዳሬክተሯ ማንኛውም ዜጋ የሚጠበቅበትን መረጃ ካሟላ አገልግሎቱን ማግኝት መብቱ ነው ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 03 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply