የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ መስኮች ተማሪዎቹን ማሰልጠን መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ለተወሰኑ ጊዜያት አቋርጧቸው የነበሩ የአብራሪዎች፣ የቴክኒሺያኖች፣ የአስተናጋጆች እንዲሁም ለሌሎች ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የገጽ-ለገጽ ትምህርት በአሁኑ ሰዓት መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

ትምህርቱ ቀደም ብሎም በቴክኖሎጂ ታግዞ እንደቀጠለ የተናገሩት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ዳይሬክተሩ አቶ ካሳዬ ይማም የቴክኒክ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን እና ቀጥታ በተግባር መማር የሚገባቸውን ትምህርቶች በልዩ ጥንቃቄ መሰጠት እንደጀመረ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ ለትምህርት የታደሙ 1 ሺ ተማሪዎች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ካሳዬ ከመስከረም ጀምሮ 137 አዳዲስ ተማሪዎችን መቀበላቸውን ጠቅሰው በቀጣይ ሩብ ዓመትም ተማሪዎችን የሚቀበሉ ቢሆንም የማስተማሪያ ክፍሎች ውስጥ የተማሪዎች ቁጥር የተገደበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

**************************************************************************

ቀን 27/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply