የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእቃ ማጓጓዝ (ካርጎ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በ7 ደረጃ ላይ ተቀመጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእቃ ማጓጓዝ (ካርጎ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በ7 ደረጃ ላይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአስደናቂ ሁኔታ ከፍተኛ እድገት በማሳየት በእቃ ማጓጓዝ (ካርጎ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በ7 ደረጃ ላይ መቀመጡን ሴንተር ኦፍ አቪዬሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእቃ ማጓጓዣ ትራንስፖርት በተለይ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት አስደናቂ እድገት በማስመዝገብ በ7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ ነው የተነገረው።

አየር መንገዶች ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተፅዕኖ በተለያየ መንገድ ምላሽ ሰጥተዋል ነው ያለው መረጃው።

ከእነዚህም መካከል በፈረንጆቹ 2019 ሁለተኛ ደረጃ ላይ የነበረው እና አሁን ላይ ቀዳሚ የሆነው የኳታር አየር መንገድ ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘመነ ኮሮና ወረርሽኝ ወቅት የ3 ነጥብ 6 በመቶ እድገት በማስመዝገብ ከቱርክ እና ሉፍታንዛ አየር መንገዶቸ ቀድሞው ሊቀመጥ ችሏል።

በ2019 በእቃ ማጓጓዝ (ካርጎ) ትራንስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ20ዎቹ ውስጥ ላልነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ስኬት ነው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእቃ ማጓጓዝ (ካርጎ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በ7 ደረጃ ላይ ተቀመጠ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply