የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመላው ዓለም ወደ ኢትዮጵያ ለሚደረገው “ታላቅ ጉዞ ወደ አገር ቤት” የ30% ቅናሽ ማዘጋጀቱን አስታወቀየኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመላው ዓለም ወደ ኢትዮጵያ ለሚደረገው “ታላቅ ጉዞ ወደ አገር ቤት” የ30% ቅናሽ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች “የ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት ጥሪ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር ይፋ የሆነውን 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡

አየር መንገዱም ይህን ተከትሎ በዛሬው ዕለት “ከአሁን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 11 2014 ተመዝግበው ትኬትዎን ይግዙ።

ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 2014 ይጓዙ” ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply