የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው በጀት ዓመት ከ5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮ…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው በጀት ዓመት ከ5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አስታውቀዋል።

አቶ መስፍን ለኢዜአ እንደገለጹት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎቱን በማሳደግና ተጽዕኖዎችን በመቋቋም ባለፈው በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም አየር መንገዱ በሰጣቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ከ66 በላይ የበረራ መዳረሻዎች ላይ አገልገሎት እየሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቶጎው ስካይ፣የማላዊ፣ የዛምቢያ፣ የኮንጎ እና የናይጄሪያ አየር መንገዶች ስኬት እንዲያስመዘግቡ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply