የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሴራሊዮን በረራ ጀመረ፡፡

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ሴራሊዮን 64ኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻ ሆነች።
በዛሬው እለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፍሪታዎን ሴራሊዮን ለመብረር የሚስችላት ስምምነት በማድረግ በረራውን ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከጊዜ ወደጊዜ መዳረሻዎችን በመስፋት ላይ ሲሆን በዛሬው እለት ፍሪታዎን ሴራሊዮን 64ኛው የመዳረሻ ሆና ሰፍራለች።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃና በአፍሪካ አህጉር በረራዋን ማስፋቷ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣በኢኮኖሚ እንድንቀራረብና እንድንተሳሰር በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።

በዚህም አየር መንገዱ በዛሬው እለት አንድ ብሎ ወደ ሴራሊዮን ፍሪታዎን በረራውን የጀመረ ሲሆን በረራው በሳምንት ሶስት ጊዜ ይሆናልም ተብሏል።

ኢትዮጵያ የበረራ አድማሷን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማስፋት ላይ እንደምትገኝና በቀጣይም ወደ ሌሎች የአፍሪካና አለም አቀፍ ሃገራት መዳረሻዋን ለማስፋፋት እቅድ እንዳላትም ተገልጿል።

በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለምአቀፍ ደረጃ ከ136 ሀገራት በላይ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በአፍሪካ ደግሞ 64 መዳረሻዎች አሉት።

በልዑል ወልዴ

ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply