የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህሬን አቋርጦት የነበረውን በረራ በዚህ ሣምንት መጨረሻ ሊጀምር ነው

ዕረቡ ሰኔ 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህሬን አቋርጦት የነበረውን በረራ በዚህ ሣምንት መጨረሻ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት መሪ አምባሳደር አወል ወግሪስ በባህሬን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ወኪል ሰለሞን ዳዊትና ባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሣምንት 3 ቀን ወደ ባህሬን የሚያደርገውን በረራ በዚህ ሣምንት መጨረሻ በፈረንጆቹ ሐምሌ 3 ቀን 2022 እንደሚያደርግ ተገልጿል።

አየር መንገዱ በኮቪድ – 19 ምክንያት በረራውን አቁሞ የነበረ ሲሆን፤ በረራውን እንደገና መጀመሩ በኹለቱ አገራት መካከል የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ያጠናክል ተብሏል፡፡

በተለይም ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ሲሄዱ ሲደርስባቸው የነበረውን እንግልት ያስቀራል ሲሉ አምባሳደር አወል ወግሪስ መናገራቸውን በባህሬን ከኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply